ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሁለት ቀናት በሱዳን ካርቱም ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው

ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናናከር የሚያስችሉ ውይይቶችን ያደረጉት፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር ጋር በሱዳን ብሄራዊ ቤተመንግስት በጋራ በሰጡት መግለጫ ፍሬያማ ውይይቶችን ማድጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታከናውናቸው የልማት ተግባራት የታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ጉዳት የማድረስ ፍላጎት እንደሌላቸውም አረጋግጠዋል፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለተካሄደው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ውጤታማና በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎች የተገኙበት እንደነበርም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይት በሰዳን የታሰሩ አትዮጵያውያን እንዲለቀቁ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በርካታ ኢትዮጵያን እንዲፈቱ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ጠንካራ የምጣኔ ሀብት ውህደትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስምምነቶች መድረሳቸውንም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በህዳሴ ግድብ ላይ ሱዳናውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ያረጋገጡበት ነበር ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here