#ዙምራ_ፋክት

እኚህ በፎቶ የምትመለከቷቸው ጥንዶች ፍቅራቸው አገር ጉድ ያሰኘ ነበረ፡፡

ይህን አንድነታቸውን በትዳር ያስተሳስሩ ዘንድ ዴቪድ ተንበርክኮ አግቢኝ ይላታል እሷም በደስታ እሺ አገባሀለው አለችው፡፡

ታዲያ ይህ ደስታቸው ገና ሳይበርድ ዴቪድ አግቢኝ ባላት እለት ታማ ሆስፒታል ትገባለች፡፡

የእርሷ ትልቅ ህልሟ ከዴቪድ ጋር በደስታ መኖር ነበረ ሆኖም ግን ህልሟ በህመሟ ተተክቶ ሆስፒታል ተኛች፡፡ በሽታዋ ቀላል አልነበረም (የጡት ካንሰር) ነበረ፡፡

ሀኪሞች ዴቪድን ጠርተው እጮኛህ ልትሞት ውስን ቀናት ቀርተዋታል ብለው አረዱት የሚያፈቅራትን የአይኑን አበባ ውዱን ማግባት ህልሙ የነበረው ዴቪድ ይህንን አደረገ የሰርጋቸውን ቀለበት ይዞ

ከአጃቢዎቹ ጋር መጣ እርሷም ሆስፒታል አልጋ ላይ ቬሎዋን ለበሰች ሁሉም በእንባ እየተራጨ ዴቪድ ፍቅረኛው ሳትሞት በቀራት ሰአት የምትመኘውን አረገላት አገባት፡፡

ሙሽሪት ደስታዋን አጣጥማ የህይወቷ ትልቅ ህልሟ ተሳክቶላት ከአራት ሰአታት ቦሀላ ላትነቃ አሸለበች፡፡

ፍቅር እንዲህ ነው፡፡ ያፈቀርከው እንደሚኖር ብቻ ሳይሆን እንደሚሞትም እያወክ አብረኸው ለመኖር ትወስናለህ፡፡

ውዶቻችን መቼ እንደሚያልፉ አናውቅም ቢያንስ የጠየቁንን ለማድረግ ይቅር ለማለት ሰአታት አንፍጅ በህይወት ውስጥ ሰአት ዋጋ አላትና!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here