ደበበ ለቁመት አልታደለም፡፡ አጭር ሰው ነበር፡፡ እጅግ በጣም አጭር፡፡ ድንክ የሚባል ዓይነት፡፡ ምክንያቱ የገባኝ ዘግይቶ ነው፡፡

በሕጻንነቱ የልጅነት ልምሻ የተባለው በሽታ የዕድገት ሆርሞኑን አጥቅቶት ነበር፡፡

አሌክሳንደር ፖፕም ቁመቱ 5 ፊት እንኳን የማይሞላ 4.6 ፊት ነበረ።

አይነቱ ቢለያይም አሌክሳንደርም በልጅነቱ በህመም ተጠቅቶ ነበር።

በ12 አመቱ የተጣባው የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ፣ አጥንቶቹን አመንምኖ ፣ አጭር አድርጎ አስቀረው።

ነገር ግን ሁለቱም አጭር ቁመታቸው በየሀገራቸው ታላላቅ ገጣሚያን ከመሆን አላገዳቸውም።

ሌላው ድንክ ፒተር ዲንክሌጅ Game of Thrones ላይ ድንኩን ቲርዮን ላኒስተርን ሆኖ የሚተውነው ተዋናይ ነው።

ፒተር 1.35 ሜትር ብቻ ይረዝማል። ፒተር በልጅነቱ እና በወጣትነቱ ፣ በዚህ ድንክነቱ የተነሳ ምሬት ይሰማው እንደነበር ያስታውሳል።

አሁን ግን ፒተር እንዲህ ይላል፦

” ከእንግዲህ ወዲያ ይህ የኔ ችግር አይደለም ፤ የነሱ ነው”

የ50 አመቱ ፒተር ዲንክሌጅ አሁን ትልቅ ቦታ መድረስ እንደሚቻል ለድንኮች ተምሳሌት/አርአያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here