የብድሩ ተጠቃሚነት መስፈርቶች

ማንኛውም በውጭ ሀገር የሚኖር/የምትኖር እድሜው/ዋ 18 እና ከዚያ በላይ ዓመት የሆነ/የሆነች
ማንኛውም አመልካች ማመልከቻወን በሚያስገባበት ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች አያይዞ ማስገባት ይጠበቅበታል

ባለበት ሀገር (በቀጠር) የመኖሪያ/የስራ ፍቃድ (መታወቂያ ካርድ)

የታደሰ ፓስፖርት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ

ሁለት በቅርብ የተነሳ/ችው ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ

የጋብቻ ሰርተፊኬት ወይም ከጋብቻ ነፃ ሰርተፊኬት

የውክልና ማስረጃ ከተወካዩ መታወቂያና ቅጂ እና ሁለት የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች

የደመወዝ መጠን የተጠቀሰበት የቅጥር ደብዳቤ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት

የቅጥር ኮንትራት ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት

በሚኖሩበት ሀገር ከሚጠቀሙበት ባንክ የአንድ አመት የባንክ ስቴትመንት

አመልካቹ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ከሆነ

የ3 ተከታታይ አመታት የባንክ ስቴትመንት

የታደሰ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ ወረቀት

የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት

አመልካቹ የዳያስፖራ አካውንት በመክፈት ሊገነባ ወይም ሊገዛ የታሰበውን ቤት ወጪ 20 በመቶ በውጭ ምንዛሪ በተከፈተው አካውንት ውስጥ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል

ባንኩ ለቤት ግንባታው አልያም ግዢው እስከ 80 በመቶ ድረስ ያበድራል

ብድሩ የሚከፈለው በአሜሪካን ዶላር፣ በዩሮ እንዲሁም በፓውንድ ይሆናል

አካውንት የሚከፈትበት መንገድ

አመልካቾች የቁጠባ ሂሳቡን ባቅራቢያቸው በሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አልያም በሚገኙበት ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በመገኘት መክፈት ይችላሉ።

መስፈርቶቹን ያሟሉ አመልካቾች የብድር ጥያቄያቸውን በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚሰራው ክፍል በመገኘት ማቅረብ ይችላሉ

የብድር አገልግሎቱ (mortgage loan) ባህሪያት

አላማ – ለቤት

ግዢ ወይም ግንባታ የሚውል

የብድር ክፍያው ቆይታ – እስከ 20 ዓመት

አነስተኛው ተቀማጭ – የቤት ግንባታ ወይም ግዢውን 20 በመቶ

የወለድ ምጣኔ – በዓመት ከ8.5 በመቶ ጀምሮ

በማንኛውም ወቅት ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ብድሩን መዝጋት ይቻላል።
#commercialbankofethiopia #diasporamortageloan
http://www.combanketh.et/MediaCenter/BroachersandFlyers.aspx

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረገጽ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here