ኢትዮ ቴሌኮም ለቅድመ ክፍያ የሞባይል ተጠቃሚዎች የዓየር ሰዓት የብድር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የቅድመ ክፍያ ሞባይል የአየር ሰዓት ብድር አገልግሎት ደንበኞች ሂሳብ በማይኖራቸው እና

በአቅራቢያቸው የቅድመ ክፍያ የሞባይል ካርድ በማያገኙበት ጊዜ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የአግልግሎት ዓይነት ነው ተብሏል።

በአገልግሎቱም ከአምስት ብር ጀምሮ እስከ 100 ብር መበደር የሚችሉ ሲሆን ካርድ በሚሞሉበት ወቅት እንደሚቆረጥ ተነግሮዋል፡፡

በዚህም ለሦስተኛ ወገን ሂሳብ ማስተላለፍ ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችንም ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በድጋሚ የብድር አገልግሎቱን ለማግኘትም ተጠቃሚዎች የመጀመሪያውን ብድር መክፈል እንደግዴታ ማስቀመጡን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘትም ተጠቃሚዎች ቢያንስ ለአንድ ወር የሰላሳ ብር የአየር ሰዓት ሞልተው የሞባይል አገልግሎት የተጠቀሙ መሆን ይገባቸዋል ተብሏል፡፡

ብድሩን ለማግኘትም A, L ወይም C ብለው ወደ 810 በመላክ የአገልገግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here