ኢትዮ-ቴሌኮም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 27 ነጥብ 7 ቢልየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከተገኝዉ ገቢ 75 ነጥብ 3 በመቶዉን የሚሸፍነዉ ከሞባይል አገልግሎት የተገኘ መሆኑን ገልጿል።

በበጀት ዓመቱ 19 አዳዲስ ምርት እና አገልግሎቶችን ለገበያ ያቀረበ ሲሆን፥ ደንበኛን የሚያረኩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን ማካሄዱን አንስቷል።

ለአገልግሎት ለገበያ ከቀረቡት ውጥትም ዳታ ካልኩሌተር፣ የመደበኛ ስልክ ጥቅል፣ የሞባይል ድምጽ፣ ጥቅል እና የድምጽ ትራንዚት ጥሪ ይገኙበታል።

አለም ዓቀፍ የድምጽ ጥሪ ማጭበርበሮችም በስራ አፈጻጸም እና በኩባንያው ገቢ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደሩም በመግለጫው ጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት የኩባንያው ደንበኞች ቁጥር 66 ነጥብ 2 ሚልየን የደረሰ ሲሆን፥ ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የደንበኞቹ ብዛት በ17 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here