ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሁን ሰሜን ጎንደር እየተባለ በሚጠራው ዞን ጠዳ ወረዳ ማክሰኚት ከተማ በ1958 የተወለዱ ሲሆን፥ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባትም ነበሩ።

የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በእንፍራንዝ የተከታተሉት ኢንጂነር ስመኘው፥ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወልድያ ከተማ ተከታትለዋል።

ከዚያም 1989 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና ትምህርት ክፍል የመጀመያ ዲግሪያቸውንም አግኝተዋል።

ከ1978 ጀምሮ በቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ይሰሩ የነበረ ሲሆን፥

እስክ 1986 ዓ.ም በተቋሙ የኮተቤ ማሰልጠኛ መምህር የነበሩ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ኢንጂነር ስመኘው ከ1986 እስከ 1988 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥራት ቁጥጥር ኢንስፔክተር፣ ከ1990 እስክ 1991 ዓ.ም በቀድሞ የኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽኑ

የስልጠና መምህር፣ ከ1992 እስከ 1996 ዓ.ም በግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከቢሮ መሀንዲስ እስከ ዋና መሀንዲስነት በመሆን አገልግለዋል ።

ከዚያም ከ1998 እስከ 2002 አ.ም የግልገል ጊቤ ቁጥር ሁለት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል።

በመጨረሻም ከ2003 ዓ.ም ዛሬ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ነበሩ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here