ሁሴን ከድር

አቶ ወልደገብርኤል አሰጌ ከ50ዓመት በፊት በንጹሕ ሕሊና በሚዛናዊ አመለካከት፣ በቅን ሃሳብ ተነሳስተው ይህን “የነብዩ ሙሐመድ አጭር የሕይወት ታሪክ” መጽሐፍ ለሰፊው ሕዝብዎ በማቅረብዎ እናመሠግንዎታለን፡፡

የእምነት ተጽእኖ ሳይጫንዎ፣ የዘመኑ አመለካከት መንፈስዎን ሳይጫንዎ ልቦናዎን ክፍት አድርገው እውነታውን ለመፈተሽ ተግተው በመሥራትዎ በድጋሚ እናመሠግንዎታለን፡፡

ነብዩ ሙሐመድ እንዳሉት “እውነተኛ ሰው ማለት እውነትን መናገር በሚያስፈራበት ቦታና ጊዜ እውነቱን መናገር መቻል ነውና” እርስዎም የሳንሱር ጣጣን አሸንፋለሁ ብለው ደፍረው በዘመኑ ይህን መጽሐፍ ማበርከትዎ ጀግንነትዎን ነውና የሚያሳየንና እናመሠግናለን፡፡

ኑረዲን ኢሳ ጊዜህን ሰውተህ ወልደገብርኤልን አፈላልገህ ስላገኘህልንና ስላስተዋወቅከን ለአንተም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ብዕርህ አይንጠፍ፡፡

ቅዳሜ ኅዳር 23 ቀን በሸገር የጫወታ ፕሮግራም የትዝታ ዘአራዳ አዘጋጅ ተፈሪ ዓለሙ የወልደ ገብርኤል አሰጌን መጽሐፍና ሥራ በማስተዋወቅህ ላንተም ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፡፡

ጅብሪል አያሌው ከሶስት ዓመት በፊት ይህንን መጽሐፍ ጎርጉረህ አምጥተህ ስለሰጠኸኝ አንተንም አመሠግናለሁ፡፡

ቅንነት ለዘላለም ይኑር!!

በቅርቡ የአቶ ወልደገብርኤል አሰጌን ድምጽ እንደምንሰማ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here