የካቲት 9/2008 ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡00 ገደማ ይሆናል፡፡

አቤል አበባውና ዘሪሁን ግርማ ከሌሎች ግብረአበሮቻቸው ጋር ሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ሰንጋ ተራ በሚገኘው የትራፊክ መብራት አካባቢ የዕለት ግዳያቸውን ፍለጋ ላይ ናቸው፡፡

እንደ አጋጣሚ ዶክተር ቴዎፍሎስ ስታማቲስ ኩንሲቲኖን መረባቸው ውስጥ ገቡላቸው፡፡

አንደኛው ተከሳሽ በጩቤ ሆዳቸውን ወጋ ፤ ሌላኛው ደግሞ ገፍተሮ መሬት ላይ ጣላቸው፡፡

በቡጢና በእርግጫ ኃይል ካሳጧው በኋላ ኪሳቸው ውስጥ ያገኙትን የዋጋ ግምቱ 11 ሺህ 700 ብር የሆነ ተንቀሳቃሽ ስልክና 200 ብር የያዘ ቦርሳ ይዘው ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡

ግለሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉም በኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 671/2 ስር የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ተላልፈው በፈጸሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡለትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች አግባብ ካላቸው የሀገሪቱ ህግጋት ጋር አገናዝቦ እያንዳንዳቸው ላይ የ14 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኖባቸዋል፡፡

ምንጭ ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here