ቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ

 የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ለኢህአዴግ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል፡፡

 ጉባኤው የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድ አድርጎ ለመምራት ወሳኝ ነው፡፡

 ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ወዳጅነት ስላለን የልምድ ልውውጥ እናደርጋለን፡፡

 የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ከኢህአዴግ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል፡፡

 ኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጂያዊ የትብብር ግንኙነት አላቸው፡፡

 በኢህአዴግ አመራር ስር በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል፣ ኢህአዴግ የህዝቦችን ኑሮ ለመለወጥ ጥረት አድርጓል፣ አሁን አገሪቱ በትራንስፎርሜሽን ላይ ናት፡፡

የጅቡቲ ናሽናል ዴሞክራቲክ ፓርቲ

 ኢህአዴግ ወጥነት ያለው አቋም ያለው ግንባር ነው፡፡

 ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊና የበለጸገች አገር ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡

 ኢህአዴግ ኢንቨስትመንትንና ግብርናን በማስፋፋት የህዝቦችን ኑሮ እንዲቀየር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል

የሩዋንዳ RPF ፓርቲ

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ውስጥ ላመጡት ለውጥ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
 አገራችን ሩዋንዳ ውስጥ ችግር ተከስቶ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ላሳያችው አጋርነት ምስጋና ይገባታል፡፡

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሩዋንዳ ለከፈሉት መስዋዕትነትና የሩዋንዳ ህዝብ ታሪክ አካል በመሆንዎ እናመሰግናለን፡፡

 ውቢቷ የሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ማሳያ ናት፡፡

 ሀዋሳ ስንሆን አገር ቤት ሩዋንዳ እንዳለን ሁሉ ነው የሚሰማን፡፡

የኬንያ ጁብሌ ፓርቲ

 ፓርቲያችን ለኢህአዴግ አጋርነቱን የገለጸበት መድረክ ነው፡፡

 ይህ መድረክ የብዝሃነት አንድነትን የታዘብንበት መድረክ ነው፡፡

 የብዝሃነት አንድነት ለፖለቲካ መረጋጋትና ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ነው፡፡

የደቡብ አፍሪካ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ

 ኢህአዴግ ላደረገው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን እናደንቃለን፡፡

 በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈረመውን የሰላምና የወዳጅነት ስምምነትን እናደንቃለን፡፡

 የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ይፈልጋል፡፡

የቬትናም ኮሚዩኒስት ፓርቲ

 ቬትናምና ኢትዮጵያ የቆየ ወዳጅነትና ግንኙነት አላቸው፡፡

 በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው የኢኮኖሚ እድገት፣ ዴሞክራሲና የህዝቦች ተጠቃሚነት በኢህአዴግ አመራር የመጣ ለውጥ ነው፡፡

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ

 ጀርመን የኢትዮጵያ ወዳጅ ናት፡፡

 ከኢህአዴግ ጋር በቅርበትና በትብብር እንሰራለን፡፡

 ኢትዮጵያ የመጣውን የፖለቲካ ለውጥ ጀርመን ትደግፋለች፡፡

 በጀርመን ሶሻል ዴሞክራሲ ውስጥ ፓርቲያችን ሁሉን አቀፍና አካታች እንዲሆን እንሰራለን፡፡

የታንዛኒያው ቻማ ቻማ ማፒንዱዚ ፓርቲ

 ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቤታችን ነው፡፡

 ቅድመ አባቶቻችን አፍሪካን በፖለቲካ ረገድ አፍሪካ ነፃ አውጥተዋል፤ አሁን እንደ ዶ/ር ዐቢይ ያሉ መሪዎች አፍሪካን በኢኮኖሚ ነፃ ማድረግ አለባቸው፡፡

 በኢትዮጵያ የታየው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ድንቅ ነው፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here