ከቀናት በፊት በአሜሪካ ሳውዝ ካሮላይና ግዛት ከታች ፎቶውን የምትመለከቱት “ከነጭ በላይ ላሳር” በሚል የዘረኝንት መንፈስ የተለከፈ የ21 አምት ወጣት አንድ የብዙዎችን ልብ የሰበረ አስከፊ ወንጀል ፈጸመ::ወንጀሉን ሲዘጋጅበት ነው የከረመው::

” በአሜሪካ የጥቁርና የነጭ ጦርነት ለመጀመር” በሚል ሽጉጥ ገዝቶ ጦርነቱን ለመጀመር ወደ አንድ ጥቁሮች ወደሚያመልኩበት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ሄደ::

በቤተክርቲያን ውስጥ ሰዎች መጽሃፍ ቅዱስ እያጠኑ ነው:: “እንኳን ደህና መጣህ ቁጭ በልና ከእኛ ጋር መጽሃፍ ቅዱስ አጥና” ብለው በፍቅርና በፈገግታ ተቀበሉት ::

ሽጉጡን በጉያው ይዞ መጽሃፍ ቅዱስ ከሚያጠኑት ጥቁሮች ጋር ቁጭ ብሎ መስማት ቀጠለ::

በዚህ ሁኔታ ለ 1 ሰአት ያክል አብሮአቸው ከቆየ በኋላ ከመቀመጫው ተነሳ, ሽጉጡን ከጉያው አውጥቶ አብረውት መጽሃፍ ቅዱስ ሲያጠኑ ከቆዩት ውስጥ 9ኙን ሰዎች በጥይት መትቶ ገደላቸውና መኪናውን አስነስቶ ወጣ::

ይህን አሳዛኝ ወንጀል ፈጽሞ በፖሊስ እጅ ከገባ በኋላ ፍርድ ቤት ቀረበ:: የተጎጂ ቤተሰቦችም አብረው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ዳኛው የተጎጂ ቤተሰቦችን “የምትናገሩት ነገር ካለ መናገር ትችላላችሁ” ብሎ እድል ሰጣቸው::አለም በጉጉት ነበር ይህን ንግግር የሚጠብቀው::

ሁሉም ሰው የጠበቀው የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲህ ይላሉ ብሎ ነበር” ይህን አረመኔ ሰይጣን ቆራርጣችሁ ጣሉት:: ሞት ይገባዋል:: ወገኖቻችንን አሳጥቶናል ::

ሃዘናችን ከፍ ያለ እና ሊገለጽ የማይችል ነው:: ሞት ለሱ ሲያንሰው ነው :: ተሰቃይቶ ሲሞት በአይናችን ማየት እንፈልጋለን…..” የሚለውን ነበር:: ይህ ግን አልሆነም ::

Nadine Collier የምትባል የሟች ልጅ ብድግ ብላ “ይቅር ብየሃለሁ, አውቃለሁ እናቴን ከዚህ በኋላ አላገኛትም , እንደበፊቱ አላወራትም ,አላቅፋትም ግን ይህም ቢሆን አንተን ይቅር ብዬሃለሁ , ለነፍስህም ይቅርታን እለምናለሁ::

ከባድ ጉዳት አድርሰህብኛል እኔን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ጉዳት አድርሰህብናል ግን ይቅር ብየሃለሁ::

( “I forgive you,” Nadine Collier, daughter of victim Ethel Lance, said to Roof. “I will never talk to her ever again, never be able to hold her again. I forgive you and have mercy on your soul. You hurt me, you hurt a lot of people, but I forgive you.”)

Alana Simmons,የተባለች የሌላኛው ሟች የልጅ ልጅ ደግሞ ተነስታ “ጥላቻ አያሸንፍም, አያቴ እና ሌሎች ሟቾች በጥላቻ እጅ ተገድለዋል::

ይሁን እንጂ ሁላችንም ለነፍስህ መዳን እንማልዳለን, ይህ ደግሞ ወገኖቻችን ለፍቅር እንደኖሩ እና እኛም በፍቅር እንደምንኖር ማሳያ ነው”

(“Hate won’t win,” she said. “My grandfather and the other victims died at the hands of hate. Everyone’s plea for your soul is proof that they lived in love and their legacies live in love.”) በማለት አለምን የሚያስደምም የይቅርታ ንግግር አድርገዋል::

አለም በሙሉ መነጋገሪያ ያደረገው ይህ የይቅርታ ንግግር አስገራሚ ነበር:: የሚከብድ እውነት!!::

ትናንት የCNN ጋዜጠኛ ወልፍ ብሊትዘር ለአንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ይህንኑ አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ” ክርስትና መሰረቱ ይቅርታ ነው::ሰዎቹ ያደረጉትም ይህንኑ ነው::

የሆነው ሁሉ በእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኗል ብለን እናምናለን:: ሰዎች ሁሉ ይህን ሲያዩ ይህ እምነት እውነትም የሆነ የተለየ ነገር እንዳለው እንዲጠይቁ ያደርጋቸዋል” ብሏል:: አስገራሚ ነው::

በሆነ ባልሆነው ከሰዎች ጋር ተጋጭተን ይቅርታ ማድረግ ተራራ የሆነብን ከዚህ ምን ልንማር እንችላለን?
ሼር በማድረግ በዚህ ፁሁፍ ጎዋደኞቻችሁን አስተምሩ ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here