በ1955 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ልደታ በተባለ አካባቢ ነው የተወለዱት፡፡

ወ/ሮ ሙሉ ባለትዳርና የ2 ልጆች እናት ናቸው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወላጅ አባታቸው በጠና ይታመማሉ፡፡

የአባታቸውን ህይወት ለማትረፍም ደም እንደሚያስፈልግ በሃኪማቸው ይነገራቸዋል፡፡ ይህ አጋጣሚ 
ለመጀመሪያ ጊዜ ደም ለመስጠት ዕድል እንደፈጠረላቸው ወ/ሮ ሙሉ ይናገራሉ፡፡

ወ/ሮ ሙሉ ወንድራድ ከዚህ ቀን ጀምሮ በተለያዩ የጤና መታወክ ምክንያቶች ህይወታቸው አደጋ ላይ ለሆኑ ለሚያውቋቸውና ለማያውቋቸው ግለሰቦች በተደጋጋሚ ደም ለግሰዋል፡፡

በዚህም በ55 ዓመት የእድሜ ዘመናቸው ለ45ኛ ጊዜ ደም በመለገስ የበርካታ ህሙማንን ህይወት መታደግ ችለዋል፡፡

ወ/ሮ ሙሉ ደም ከመለገስ አልፈው ደም መለገስ ለሰው ልጆች በተለይም የእናቶችንና ህጻናትን ህይወት ለመታደግ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ግንዛቤ በመፍጠር ከፍተኛ
አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡

ደም መለገስ የህሊና እርካታ እንደሚሰጥ የሚናገሩት ወ/ሮ ሙሉ የሚተካውን ደም በመለገስ የማይተካውን የሰውን ልጅ ክቡር ህይወት መታደግ እንደሚቻል ምስክር ናቸው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here