ወ/ሮ ቢልለኔ ሥዩም በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የፕረስ ሴክረታሪ ኃላፊ፤ ወ/ሮ ሄለን ዮሴፍ ደግሞ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

አቶ ሽመልስ በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት የፕሬስ ሴክቴሪያት ጽ/ቤት፣ የብቃትና ፖሊሲ ሚዘና ጽ/ቤት፣ የአገር ደህንነት ጉዳይ አማካሪ ጽ/ቤትና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትን ይመራሉ፡፡

አቶ ሽመልስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰብአዊ መብት የማስተርስ ዲግሪ፣ ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝ አፍሪካ (UNISA) ፖስት ግራጁየት ዲግሪ በፖለቲካል ፊሎሶፊ አግኝተዋል፡፡

ፕረስ ሴክሬታሪዋ በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሃገር ውስጥና ለውጭ ሃገር ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ከጋዜጠኞቹ ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ለተነሱላቸው ጥተያቄዎች በሰጡት ምላሽም የፕረስ ሴክሬታሪው የቀድሞውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት ተክቶ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ለህዝቡ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ እንደሚሰራም ነው የተናገሩት።

በቅርቡም የፕረስ ሴክሬታሪውን አወቃቀርና አደረጃጀት በተመለከተ በቅርቡ ማብራሪያ ይሰጣል ብለዋል።

The Press Secretariat department at PM ‘s office will be led by and her deputy .

Both Billene & Helen have extensive experiences in communications & journalism. The new Chief of Staff, Shimelis Abdissa will oversee the PS department.

የመንግስትን እቅድ በግልጽ ቋንቋ ለህዝብ ለማድረስ ባለ አንድ ገጽ የእቅድ ሰሌዳ ይፋ ተደረገ።

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ነው ባለ አንድ ገጽ እቅዱ ይፋ የተደረገው።

አቶ ፍጹም አረጋ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንደሚሾሙ ተገለጸ

የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ ወደ ቀድሞ መስርያ ቤታቸው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንደሚመለሱ በቲውተር ገጻቸው አስታውቀዋል::

በታሪካዊ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወቅት የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በማገልገላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል::

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያደርሱ ጥርጣሬ እንዳሌላቸውም ጨምረው ገልጸዋል አቶ ፍጹም አረጋ::

ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተሰጠ ያለውን ጋዜጣዊ መግለጫ ቀጥታ ይከታተሉ

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Monday, November 5, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here