የቀድሞ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የሕግ ባለሞያ(ጠበቃ)፣የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣

የአንድነት ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር እንዲሁም የቀድሞ የፖለቲካ እስረኛ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በመንግሥት ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ መሆኑን ምንጭች ነግረውኛል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ስመጥር ከሆነው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር (Public Administration) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተቀበሉት ወ/ት ብርቱካን

ዕረቡ ጥቅምት 28/2011 ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተው፤

ሐሙስ ጥቅምት 29/2011 ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ታውቋል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙትም መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት መሆኑ ታውቋል።

#Ethiopia #BirtukanMideksa

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here