“ከባዱን ሥራ እንዲሰራ ሰነፉን ሠራተኛ መረጥኩኝ፡፡ ምክንያቱም ሰነፍ ሠራተኛ ከባዱን ሥራ ለመስራት ቀላል መንገድ መፍጠር ይችላል፡፡”

“ደሃ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም፡፡ ደሃ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው፡፡”
.
“በእጅህ ገንዘብ ሲኖር ራስህን ትረሳለህ፡፡ በእጅህ ምንም ገንዘብ ሳይኖር ሲቀር ደግሞ ዓለም ማን እንደሆንክ ይረሳሃል፡፡ ሕይወት ማለት እንደዚህ ነው።”

“በትምህርት ቤት ቆይታዬ በጥቂት የትምህርት ዓይነቶች ወድቄ ነበር፡፡

ጓደኛዬ ግን ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች በብቃት አልፎአል፡፡

አሁን እሱ በማይክሮሶፍት ኩባንያ መሃንዲስ ነው፡፡ እኔ ደግሞ የኩባንያው ባለቤት ነኝ፡፡”

“በዓለም ሳለህ ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ እንደዛ ካደረግክ ራስህን እየሠደብክ ነው፡፡”

“ስኬትን ማክበር መልካም ነው፡፡ ከሁሉ የበለጠ አስፈላጊው ነገር ግን ከውድቀት ምርጡን ትምህርት በማስተዋል መውሰድ ነው፡፡”

“ንግድ ጥቂት ህጎችና እልፍ ስጋቶች ያሉት የገንዘብ ጨዋታ ነው፡፡”

“ደስተኛ ያልሆኑ ደንበኞችህ ዋናዎቹ አስተማሪዎችህ ናቸው፡፡”

ትዕግስት የስኬት ቁልፍ መሠረት ነው፡፡”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here