ታማኝ በየነ

የዛሬ 27 ዓመት እንዲህ ብሎ ነበር

የወንድ ቅድመ አያቴ ከመንዝ ተነስቶ
በቾ ተቀመጠ አንድ ኦሮሞ አግብቶ
ያቺ ኦሮሞይቱ የኔ ሴት ቅድመአያት
ልጅ ወልዳ አሳደገች የኔን እናት አባት

ለአቅመ ሔዋንም ስትደርስ በጥሩ እንዳደገች
ከመቀሌ የመጣ አንድ ትግሬ አገባች

ይህ የአያቶቼ ልጅ ይህ የተወለደው
አባቱ ነው ትግሬ አማራ ኦሮሞ ነው

ለአቅመ አዳምም ሲደርስ አንዲት ውብ ልጅ ወዶ
ልትኖር አዲስ አበባ የመጣች ከሶዶ
ጉልቻ ጎልተው ሲኖሩ ተዋደው
አብረው ፍሬም አዩ እኔን ወንዱን ወልደው

ኦሮሞም ትግሬም ነኝ ጉራጌም አማራ
ዘሬ ማን ሊባል ነው ማን ተብዬ ልጠራ

ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቂኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው

ታማኝ በየነ 1983 @አዲስ አበባ ስቴድየም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here