13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቐለ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

“ህዝባዊነታችን የፅናናታችንና የድላችን መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባዔው የክልሉን የዕድገት አቅጣጫዎች ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት በ12ኛው የድርጅቱ ጉባዔ ተቀምጠው የነበሩ አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ይገመግማል ተብሏል፡፡

በመቐለ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት ድርጅታቸው ህገ መንግስታዊ ስርዓትና መንግስትን ለማፍረስ የሚጣጣሩ ኃይሎችን ይታገላል፡፡

በድርጅቱ የተጀመረውን ተሃድሶ ለማድርስ የክልሉ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡ በዚህኛው ጉባኤ አዳዲስ አመራሮች የሚተኩበት እና ውሳኔዎች የሚተላፉበት መድረክ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት መሻከር የተጎዳውን ህዝባችንን ለመካስ ድርጅታቸው ሌት ተቀን እንደሚተጋም አመልክተዋል፡፡

የኢህአዴግ እህት እና አጋር ድርጅቶችም በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ታድመዋል፡፡

ህወሓት ወደ ትግል ወጥቶ ለትግራይ ህዝብ ከጭቆና መላቀቅና ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያደረገው ትግል በዛሬዋ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ በአዲስ ምዕራፍ እንዲደገም ከህወሓት ጎን እንደሚቆሙም አጋርነታቸውን ገልፀዋል፡፡

በተለይም ኢህዴግ ከገባበት ቀውስ ወጥቶ በተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ ህወሓት ለሚያካሂደው ትግልና ተሃድሶ እንደሚደግፉ አመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በጉባኤው አለም አቀፋዊ፣ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች እንደሚገመገሙ ተገልጿል፡፡

13ኛው የህውሃት ድርጅታዊ ጉባዔ የድርጅቱን ሊቀመንበርና እና ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ አዳዲስ የስራ አስፈጻሚዎችና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ ለውጡን ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ዶክተር ደብረፅዮን ገለፁ

ዛሬ የተጀመረው 13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ/ህወሃት/ ድርጅታዊ ጉባኤ ለውጡን ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለፁ።

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ አሁን በሀገሪቱ በአንድ በኩል የሚታይ ተስፋ በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋውን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ስጋቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህን ስጋቶች በመቀነስ ተስፋውን ማለምለም እና የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን የህዳሴ ጉዞ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይህ ጉባኤ ትኩረት ሰጥቶት እንደሚመክር ነው የተናገሩት።

በጉባኤው ህወሃት የድርጅቱን ውስጠ ዴሞክራሲ ማስፋት በሚያስችለው መልኩ ህገ ደንቡ ላይ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።

ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እያደረጉት ካለው የአርማና ስያሜ ለውጥ አንፃር በህወሃት ዘንድ ይኖር ይሁን ተብለው የተጠየቁት ዶክተር ደብረፅዮን፥ ድርጅታቸው ለጊዜው የስያሜም ሆነ የአርማ ለውጥ እንደማያደርግ ተናግረዋል።

መተካካትን በተመለከተ ህወሃት ነባር አመራሮችን የመተካት ሂደትን ቀድሞ የጀመረ ቢሆንም፥ በአሁኑ ጉባኤ ግን ሰፋ ባለ መልኩ አዳዲስ ወጣቶችን እና ሴቶችን ወደ አመራርነት ያመጣል ነው ያሉት።

13ኛው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ የጀመረ ሲሆን፥ ከሰዓት በኋላ ጉባኤውን የሚመሩ የፕሬዚዲየም አባላት ምርጫን በማድረግ ውይይቱን በስፋት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

13ኛ የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ መድረኩን የሚመሩ የፕሬዚዲየም አባላት ምርጫ አድርጓል

13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ ድርጅታዊ ጉባኤ መድረኩን የሚመሩ የፕሬዚዲየም አባላት ምርጫ አድርጓል።

በዚህም መሰረት በእጩነት ከቀረቡት ሰባት ተጠቋሚዎች መካከል አምስቱ በአብላጫ ድምጽ በማግኘት ተመርጠዋል።

በዚህም መሰረት፦
1. ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
3. አቶ ጌታቸው ረዳ
4. አቶ አለም ገብረዋህድ እና
5. ዶክተር አርከበ እቁባይ ተመርጠዋል።

ድርጅታዊ ጉባኤው የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ነገም የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለድርጅታዊ ጉባኤው ባዘጋጀው ሪፖርት ላይ የቡድን ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የህወሃት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ ሚካኤል በድርጅቱ 13ኛው ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር

የህወሃት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ ሚካኤል በድርጅቱ 13ኛው ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር

የህወሃት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ ሚካኤል በድርጅቱ 13ኛው ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር

Posted by FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) on Wednesday, September 26, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here