እንኳን ለሀገርዎ አበቃዎት፣ወደ መስሪያ ቤትዎም በሰላም መጡ !!

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከ 32 ዓመት በኋላ የቀድሞ መስሪያ ቤታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝተዋል፡፡

እንኳን ለሀገርዎ አበቃዎት፣ወደ መስሪያ ቤትዎም በሰላም መጡ፡፡

ከ32 ዓመታት ስደት በኃላ አገራቸው የተመለሱት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ በአገራችን ታሪክ ውስጥ 20ኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው፡፡

የኮለኔል ጎሹን የቀድሞ ቢሮ ያስጎበኘሁቸው ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመካሄድ ላይ ያለውን የማስፋፍያ ግንባታም አስጎብኝቻቸዋለሁ ፡፡

ኮሌኔል ጎሹ ወልዴ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሲሆን በቀድሞ ቢሯቸው በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል ።

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ በበኩላቸው ፤ ‹‹በዛው በስደት የምቀር እንጂ ወደምወዳት አገሬ የምመለስ እንዲሁም ይሄ ጊዜ የሚመጣ አይመስለኝ ነበር›› ሲሉ በሞቀ ፈገግታ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት የአፍሪካ ቀንድን የሰላም ሁኔታ ለመለወጥ መ/ቤቱ ያደረገውን ዲፕሎማሲ አደንቃለሁ ብለዋል፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here