1. ትእቢተኛ ያደረገህ ገንዘብ ወዴት አለ?

2. ትምክህተኛና ጉረኛ ያደረገህ መልክና ቁመና ወዴት አለ?

3. ከሰው በላይ ያገዘፈህ መኪና ወዴት አለ?

4. የበላይ አለቃ ያደረገህና ሰራተኞችን አንቀጥቅጠህ እንድትገዛ አቅም የሰጠህ የሙያ ወረቀትህ ወዴት አለ?

5. ያበድክላቸው ጓደኞችህ ወዴት አሉ?

6. በመቃብር ውስጥ ምን ያህል ታምራለህ?

7. አጠገብህ ያሉትን ወገኖችህን ነፍስ አጥፍተህ ያከማቸሀው ንብረት ወዴት አለ?

ባለጠጋ መሆን መልካም ነው፤ ንብረት ማከማቸት መልካም ነው፤ መልከመልካም መሆንም ጥሩ ነው።

ነገር ግን ከሁሉ በፊት “ሰብአዊነትን አስቀድም”።

መቃብር ሀብታምና ደሀ እኩል የሚሆንበት ብቸኛ ሥፍራ ነው።

ለማወቅ ትጋ፥ ሀብትን አፍራ፥ መልክህ ላይ ስራ…ነገር ግን ከሁሉ በፊት ሰብአዊነት ይቅደም።

የህይወት ውበት ማሰብ ነው !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here