በተፈጥሯዊ መንገድ የተዘጋጁ የካስተር ኦይል፤ (የጉሎ ዘይት)  የሬትና የባሀር ዛፍ፤ ውጤቶችን  ከሀገር በቀሉ የጤናና የውበት ካምፓኒ  ኢት- ኸርባል!

አዲስ ዓመት፤ አዲስ ሃሳብ፤ አዲስ ራዕይ ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ የውበት መንገድም እንጂ ! እናም  እንደ አደይ ፍክት፤  እንደ መስከረም ጮራ ድምቅ ያለ፤ የሰውነት ውበት የሚሰጡትን ተፈጥሮአዊ  የኢት ኸርባል ምርቶች እነሆ…

 ካስተር ኦይል፤ (የጉሎ ዘይት) የሬት ሻምፑና ኮንዲሽነር ፤የሬት  የፀጉር ቅባት እና ሳሙና!

በየመንገዱ ምንጫቸው ያልታወቀ የሬት ምርቶች ሲሸጡ ብዙ ጊዜ ተመለከትኩ!

 በተለያየ አጋጣሚ  ብዙዎቹን  አድራሻቸውን እንዲያሳዩኝና አመራረቱን እንዲጠቁሙኝ ጠይቂያለሁ! ግን የሚያስገኘውን ጥቅም ከመዘርዘርና ‹‹ግዛን›› ከማለት ያለፈ መልስ አጣሁ !!

ይሄኛው አጋጣሚ ግን ይለያል ! አንድ ቀን ፒያሳ  ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በከተማ አስተዳደሩ ፊለ ፊት በሚገኘው መሸጫ ሱቃቸው ጎራ አልኩኝ!

እዛው የምትገኘውን የሽያጭ ባለሙያ ቢሮአቸውን ወይም ማምረቻቸውን ማየት እንደምፈልግ ጠየኳት ፡፡

22 ባታ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው ዋና መስሪያ ቤታቸው እንድሄድ ጠቆመችኝ !ወዲያውኑ ሄድኩ ፡፡

ከድርጅቱ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ማቲዎስ መባ ጋር ተገናኘሁ፡፡

 ሁሉንም የምርት ጥራትና የማምረት ፈቃድ አሳየኝ፡፡ ሃሳቤን  በቀናነት  ተቀብሎኝ ማምረቻው ወደሚገኝበት ወደ ጉርድ ሾላ ሄድን ! ምርቶቹ በሰለጠኑ ባለሙያዎችና በዘመናዊ መሳሪያ መመረታቸው በሀገሬ በጣም እንድኮራ አረገኝ!

አመራረቱንና ጥሬ እቃውን ስለተመለከትኩ ደስ አለኝ !ይህን ምርት የተጠቀሙ ሰዎችንም አናገርኩ … በልበ ሙሉነትም ይህን መረጃ ልጽፍላችሁ ወደድኩኝ !!

 እነዚህን ተፈጥሮአዊ የሆኑ ምርቶችን ለመጠቀም ምክንያታዊ ሆናችሁ እንድትገዙ እነዚህን ሳይንሳዊ ጥቅሞች ልጠቁማቸሁ !

የካስተር ዘይቱ  GFE global በተሰኘ እና ከሀገረ አሜሪካ በመጣ ዘመናዊ መሳሪያ የሚመረት ሲሆን ፀጉርን ለማወፈር ፤ለማርዘም እንዲሁም ለማንፀባረቅ ይረዳል !

የቆዳና የፀጉር ተፈጥሮአዊ እርጥበትን ይጠብቃል !የፀጉር መሳሳትን ይከላከላል !የቅንድብና የሽፋሽፍት ውበትን ይጠብቃል!

በሆድ በብብትና በታፋ አካባቢ የሚወጣ የቆዳ ሸንተረርን ወደ ቀድሞው ይመልሳል! ቆዳን ከድርቀት ይከላከላል ሲል በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይተነትናሉ፡፡

ምሁራኑ እንደሚያትቱት በዘመናዊ ማሽን አማካኝነት  በጥብስ ቅጠልና በባህር ዛፍ ምጥን ዘይቶች ተቀምመው የሚዘጋጁት የኢት ኸርባል የሬት ምርቶች ደግሞ የሬት ቅባት ሻምፖና ኮንዲሽነር ሲሆኑ ለፀጉር መለስለስ  መፋፋት እንዲሁም መርዘም ልዩ ገፀ-በረከቶች ናቸው ፡፡

የሬት ሳሙናው ለቆዳ ውበትና ልስላሴ በእጅጉ ይመከራል!!

በአጠቃላይ ኢት ኸርባል በሀገራችን የዘመን ቀመር በ2009 ዓ/ም  ተመስርቶ የካስተርና የባህር ዛፍ  ዘይቶችን እንዲሁም  የሬት ሻንፖና ኮንዲሽነር፣ሳሙና፣ቅባትና መሰል የሬት ውጤቶችን ለፀጉርና ለቆዳ ውበት ተስማሚ በሆነ መንገድ በሀገር ውስጥ በማቀነባበር እና በማቅረብ እየሰራ ነው!

እነዚህ የውበት መጠበቂያ ምርቶች በዘርፉ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ  ረጅም ልምድ ባለቸው ባለሙያዎችና በዘመናዊ መሳሪያዎች የሚዘጋጅ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ ምርቶቹ ከፍተኛ ተቀባይነትን አትርፈዋል፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአዳማ ድሬዳዋ እና ባህርዳር ቅርንጫፎችን በመክፈት ምርቶቹን በማከፋፈል ላይ ይገኛል!

ኢት ሐርባሎች የአዲስ ዓመትን ብስራት ተከትሎ በኤግዚብሽን ማዕከል በተዘጋጀው ባዛር ላይ በአለምችን ለውበትና ለጤና የተመሰከረለትን ካስተር ኦይልን ጨምሮ ሁሉንም ምርቶቻቸውን ይዘው ቀርበዋል !!

ልብ በሉ – ‹‹ግዙኝ›› የተባላችሁትን ሳይሆን ልትገዙ ያሰባችሁትን የውበት ምስጢር መግዛት ብልህነት ነው፡፡ ከተመሳሳይ አርቴፊሻል ምርቶች ራሳችሁን ለመታደግ ‹‹ኢት ኸርባል›› ብላችሁ ጠይቁ!

ድርጅቱ በምርቶቹ አይደራደርም፡፡ ውበትን ብቻ ሳይሆን አንዳች ቅሬታ ቢኖር 100 ፐርሰንት የገንዘብ መመለስ ዋስትናንም ደርቦ…መርቆ ይሰጣል!

የውበትና የጤና ቀጠሮ የለውምና ደውሉላቸው! 

+251 – 965 – 58 58 58

ሰላም!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here