የታጋይ በረከት ስምዖን ሁለተኛ መጽሐፍ ገበያ ላይ ውሏል።

አቶ በረከት ስምኦን መጽሐፉን የፃፋበት አንዱ ምክንያት …

‘በአንድ በኩል ሕገ-መንግስታዊ የግልፅነትና ተጠያቂነት አሠራር እየሸሸን ባለበት በዚህ ወቅት

ተገቢውን ድፍረት በማሳየት ወደ ግልፅነት ተጠያቂነት ሥርዓት ለመመለስ እንድንችል የተመረጠ አቀራረብ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌዴራልና በሁሉም ክልሎች

የምታዘበውን የማን አለብኝነት አዝማሚያ በግልፅ አደባባይ መግጠም በትዕቢት ለተሞሉ መሪዎች

የዴሞክራሲችን ወርድና ስፋት ለማሳየትና እያንዳንዳችን ለምንወስነው ውሳኔ ኋላፊነትና ተጠያቂነት እንደማይቀርልን ለማስገንዘብ ጭምር ነው፡፡

ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕሌቶ እንደለው፤ ‘የምጨነቀው ለአሁኑ ሳይሆን ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ለሚኖረው ስሜ ነው’ እንዳለው፤

ዛሬን ብቻ እያሰቡ፣ ሕይወታቸውን ያለ ትህትና ለሚኖሩና ለሚመሩ ሰዎች ሁሉ የፍርድ ቀን እዚሁ ምድር ላይ እንደሚጀምር ለማስገንዘብ ነው፡፡

ታዋቂው አልጄሪያዊውና ፈረንሳዊ ፈላስፋ አልበርት ካሙ ‘የመጨረሻው የፍርድ ቀን አትጠብቅ፣ እዚሁ በምድራችን ላይ በየቀኑ እየተፈፀሙ ነውና’ ይላል፡፡

እናም የፍርድ ቀንን ከሰማይ ሲጠብቁ ጊዜ ያላቸው ለሚመስላቸው ሁሉ ማህበራዊ ብይንን እዚሁ በምድር ላይ ከቅርባቸው እንደሚያገኙት ለማሳየትም ጭምር ነው፡፡’

ትንሳኤ ዘ-ኢትዮጵያ ከመንታ መንገድ፣ በረከት ስምኦን ((ከመግቢያው ገጽ የተወሰደ))

ገጽ 1

መታሰቢያነቱ

“ለምንጊዜም መምህሬ መለስ ዜናዊ ”

ካላንተ ይህች ኢትዮጵያ ካሸለበችበት ቀና አትልም ነበር ። ይህን የምለው የጓዶችህንና የሰፊውን ህዝበ ኢትዮጵያ ሁሉ ሚና አሳንሼ በማየት አይደለም ።

ካለነርሱ አንተም እንዲህ አትሆንም ነበርና ። ነገር ግን አንተ ልዩ ሰው ነበርክ ።

በዚህ መጽሃፍ በበቂ ሁኔታ ብገልፀውም ባልገልፀውም ፡ በተሟላውም በተነካካውም ፡

አሻራህ የሌለበት ፡ አርቆ አስተዋይነትህ ያላረፈበት ከቶ ምን ነገር ነበር ?

በርግጥ ያላንተ የማሽቆልቆሉ ጉዞ ይገታ ነበርን ? ቀና ማለትስ እንችል ነበርን ?

ታሪክ ሰሪው ሰፊው ህዝብ መሆኑ ባያከራክርም ፡

በታሪክ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ አንተን የመሰሉ ታላቅ መሪዎች በሌሉበት ሃገራችን ይህን ያህል ርቀት መጓዝ አትችልም ነበር ።

ሌትቀን ባደረግከው ጠረት ራስህን በማብቃት፣ የለምንም ስሰት በጠራ ሀሳብ ለሞላኸው አዕምሮ ምሥጋናዬ ወደር የለውም።

የተገለጠ መጽሓፍ ከመሆን በላይ ምን አለና።

እንዲሁም በኢህአፓ አባልነት ህዝባዊ ተልዕኮ ሊፈጽም ሲንቀሳቀስ ጐጃም ላይ ተይዞ በደርግ ለተገደለውና

በሂስ ውስጥ መኖር ላስተማረኝ በሪሁን ዳኘው ጋንች ና ለአሥራ ዘጠኝ ሥድሳዎቹና ሰባዎቹ የትግልና የመሥዋት ትውልድ….

( በረከት ስምኦን ፥ ትንሳኤ ዘ – ኢትዮጵያ )

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here