(በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና) #Ethiotena #CalanderMethod

ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው የወር አበባን መሠረት ያደረገ ወይም

በእንግሊዝኛ አጠራሩ ካላንደር ሜትድ (Calander Method) የሚባለውን እርግዝና ሊፈጠርና ላይፈጠር የሚችሉባቸውን ቀናቶች ለይተን ለማወቅ የሚረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲሆን

ይህ መረጃ በማወቅ ደረጃ ብቻ ቢሆንና ወደ ተግባሩ ለመሄድ አደጋ እንዳለው ከወዲሁ እንድትገነዘቡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

በትክክል እርግዝና ሊፈጠርባቸው የሚችሉት ቀናቶች ኦቪውሌሽን በሚከናወንበት ቀናቶች ናቸው፡፡

ኦቪውሌሽን (Ovulation) የሚከሰትበት ቀን አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ14ኛው ቀን አካባቢ ይከሰታል፡፡

ስለዚህ ከፍተኛ የማርገዝ ዕድል የሚኖርባቸው ቀኖች የወር አበባ በኋላ ባሉ ከ8-10 ቀኖች ነው (የወር አበባዎ ለመቆም ከ4-6 ቀኖች የሚፈጅበት ከሆነ) ፡፡

ነገር ግን ረዘም ያለ የወር አበባ ጊዜ ካለዎት ኦቪውሌሽን የሚከሰትበትም ጊዜ ስለሚረዝም የወር አበባዎን እርዝመት ማወቅ አለብዎት፡፡

የሚከተለው መረጃ ከወር አበባ በኋላ እርግዝና የሚፈጠርባቸውን ቀኖች የሚያሳይ ሲሆን መሰረት ያደረገው በየ 28 ቀን የወር አበባዋን ለምታይ ሴት ብቻ ነው፡፡

• ከቀን 1-5 (የወር አበባ ከፈሰሰበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን) = የወር አበባ መፍሰሻ ጊዜ ነው፡፡ (Menstrual Bleeding)

• ከቀን 6-9 = በንጽጽር እርግዝና የማይፈጠርበት ጊዜ ነው፡፡ (Relatively Infertile)

• ከቀን 10-12 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile)

• ከቀን 13-15 = በነዚህ ቀኖች በእርግጠኝነት እርግዝና ይፈጠራል፡፡ (Most Fertile)

• ከቀን 16-19 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile)

• ከቀን 20-28 = በነዚህ ቀኖች እርግዝና አይፈጠርም፡፡ (Infertile)

ማስታወሻ

ትክክለኛው የኦቪውሌሽን ጊዜ የሴት እንቁላል የወንድ የዘር ፍሬን ዝግጁ ሁኖ የሚጠብቅበት ጊዜ ሲሆን ይህም ጊዜ ከ 12 – 24 ሠዓት ብቻ ይረዝማል፡፡

ምክንያቱም የወንድ የዘር ፍሬ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሰውነት ውስጥ ከሶስት (3) እስከ አምስት (5) ቀናቶች መቆየት ይችላል የሴቶች ዕንቁላል ደግሞ ለተጨማሪ ቀናቶች ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ሊያረግዙባቸው የሚችሉ ከ አምስት(5) እስከ ሰባት (7) የሚደርሱ ቀኖች አሉ ማለት ነው፡፡

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here