ቃለ ምልልስ – የኦሮምያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ
ከአውራምባ ታይምስ ዳዊት ከበደ ጋር
 DAWIT KEBEDE Interviews Activist Jawar Mohammed on Current Ethiopian events and the way forward

ከጃዋር ቃለምልልስ የተወሰዱ ነጥቦች

● የትግራይ ህዝብ በቀደሙት መንግስታትም ሆነ ባለፉት 27 አመታት ምንም ያገኘው ጥቅም የለም። ቢያንስ ከዚህ በኋላ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ አብሮነታችንን እናጠናክር

● በጠ/ሚ አብይ እና መቀሌ በሚገኙት አንጋፋ የህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መቃቃር ወደ እውነተኛ እርቅ እንዲቀየር የበኩሌን ጥረት አርጋለሁ።

እውነተኛ እርቅ ተፈጥሮ እነሱም ባላቸው ልምድ አብይን ሊያግዙት ይገባል

● እነሱ (መቀሌ ያሉት) ከእልህ መውጣት አለባቸው፣ ጠ/ሚ አብይም ከዚህ በኋላ በሚያደርጓቸው ንግግሮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው

● ባለፉት 27 አመታት ብዙ መልካም ነገሮችም ጥፋቶችም ተሰርተዋል። በተሰሩ ጥፋቶች ዙሪያ ሂሳብ ማወራረድ ለማንም አይጠቅምም:: ይህ እንዲሆን ግን ሀሉም ወገን ተባባሪ መሆን አለበት

  • ሕውሃት ትግራይን የረሳ ፓርቲ ነው፡፡ ዛሬ ሥልጣን ሲያጣ ነው ትግራይ የሚገባው? …ሥልጣን ሲኖረው ትግራይን ያላስታወሰ ፓርቲ … የትግራይ ሕዝብ ለምን ይህንን አይጠይቅም!? 
  •  የትግራይ ሕዘብ ለ17 ዓመታት ታግሎ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ልጆቹን የገበረ ነው፡፡ ካለፉት 27 ዓመታት በእርሱ ሥም አገር ተጨቁኗል፡፡ ዝርፊያ ተካሂዷል፡፡ የትግራይ ሕዝብ የተጠቀመ አይደለም፡፡
  •  መንግሥት ሁሌም ሊተች ይገባል፡፡ የአክትቪስት ሥራ ሁሌም መንግስትን መተቸት ነው፡፡ አክትቪስት ከተቺነት ወደ አጨብጫቢነት ከተለወጠ ችግር ነው፡፡

28 ደቂቃ የፈጀውን ቃለ መጠይቅ ይመልከቱ …

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here