የዓለም ጤና ድርጅት በእባብ ተነድፈው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተሳበው በላይ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ከተባሉት የጤና ዝርዝሮች ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል፡፡

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ገለጻ በዓመት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በእባብ ተነድፈው ህይወታቸው ስለሚያልፍ ተኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ የጤና ጉዳዮች ውስጥ ተደርጓል፡፡

ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ለአይነ ስውርነትና ሌሎች የአካል ጉዳቶች እንደሚጋለጡ ተነግረቷል፡፡

አፍሪካዊያን ደግሞ በእባብ መነደፍ ምክንያት እጅጉን ተጎጂ ሲሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚሞቱት ሰዎች መካከልም አንድ አምስተኛ የሚሆኑት አፍሪካዊያን ናቸው፡፡

ድርጅቱ በዚህ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ያደረገውም ሃገራት የችግሩን ደረጃ በመረዳት የየራሳቸውን እርምጃ እንዲወስዱ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ከእነዚህ እርምጃዎች መካከልም የመርዙን ማርከሻ በርካሽ ዋጋ ማቅረብና ለህክምናው ስልጠናዎችን መስጠት ተካቶበታል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here