በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ትምህርት ሚኒስቴር የነበሩት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዛሬው ዕለት ወደ ሃገራቸው ገቡ።

ኮሎኔል ጎሹ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፣

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዘመነ ደርግ ከነበሩ ባለስልጣናት እጅግ ተማሩ ከሚባሉት መካከል ዋነኛው ሲሆኑ በመጨረሻዎቹ የደርግ አገዛዝ ዘመናት ደርግን በመቃወም ከሀገር ወጥተው ለ32 ዓመታት በስደት የኖሩ ናቸው።

ኮሎኔል ጎሹ ምንም እንኳን የደርግ አባል በኃላም አፈንጋጭ የፓለቲካ ስደተኛ ቢሆኑም የደርግ መንግስት በብዙዎች ዘንድ የሚደነቅበትን

«የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን እና ሉአላዊነትን አሳልፎ ያለመስጠት» ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አራማጅ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያን የፓለቲካ ታሪክ የሚያወቅ ያውቀዋል።

ኢህአዴግ ደርግን ጥሎ ወደ ስልጣን በመጣበት ማግስት ከተከሰቱ ግዙፍ ሀገራዊ ጉዳዬች መካከል የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል ነበር።

ኮሎኔል ጎሹ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሰሙ ፓለቲከኛ ናቸው።

ጉዳዮን አስመልክቶ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኤርትራ መገንጠል ምክንያት የሆነውን የህዝበ-ውሳኔ (ሪፈረንደም) መደገፍን በምሬት የተቹበት ንግግራቸው ኮሎኔል ጎሹ በታሪክ የሚወሱበትን ክስተት ፈጥሮ አልፏል።


***

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከሦስት ዓስርት ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል

~ ኮሎኔል ጎሹ በኢሉባቡር ጎሬ ከተማ በ 1935 ዓም ተወልዱ

~ በታዋቂው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሐረር ጦር አካዳሚ ሁለተኛው ምድብ ምሩቅ ናቸው

~ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል

~ ከአሜሪካ የል ዩኒቨርሲቲ በሕግና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በከፍተኛ ዉጤትና ማዕረግ ምሩቅ

~ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ከፍተኛ መኮንን

~ በቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በኮለኔልነት ያገለገሉ ምስጉን መኮንን

~ በውታደራዊ አገልገሎታቸው የክብር ሜዳሊያ ተሸላሚ

~ የኢትዮጵያ የትምህርት ምኒስትር

~ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር

~ የመልካም ባህሪይ ከሙስና የፀዱና ሃገር ወዳድነት ይታዋቃሉ።

~ በኢትዮጵያ የመሰረተ ትምህርት የፀረ መሀይምነትን ዘመቻ መሥርተው በመምራት ይታወቃሉ።

~ የወታደራዊውን መንግስት አገዛዝ በመቃወም ሥልጣናቸውን ተተው በአሜሪካ ለ 32 ዓመታት ቆይተዋል

~ የህወሃት አገዛዝን በመቃወም በአሜሪካ መድህን ፓርቲን በማቋቋም ሰላማዊ ትግል መርተዋል

~በጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አመራር በተደረገላቸው ጥሪ ከሦስት ዓስርት ዓመታት ሰደት በኋላ ሰኞ ማለዳ አዲስ አበባ ይገባሉ።

~ውዱ የኢትዮጵያ ባለውለታ ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እንኳን ለሀገርዎ አበቃዎት።

በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው ገቡ።

ኮሎኔል ጎሹ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፣

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር መንገድ በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው በመልቀቅ ላለፉት 32 አመታት ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያለውን አጠቃላይ የለውጥ ሂደት ለመመልከት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅና የተጀመረውን የሰላም፣

የፍቅርና የመደመር ሂደት በሚችሉት መጠን ለመደገፍ ወደ ሃገራቸው መምጣታቸውንም አንስተዋል።

በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ትምህርት ሚኒስቴር የነበሩት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዛሬው ዕለት ወደ ሃገራቸው ገቡ።

ኮሎኔል ጎሹ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፣

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በዘመነ ደርግ ከነበሩ ባለስልጣናት እጅግ ተማሩ ከሚባሉት መካከል ዋነኛው ሲሆኑ በመጨረሻዎቹ የደርግ አገዛዝ ዘመናት ደርግን በመቃወም ከሀገር ወጥተው ለ32 ዓመታት በስደት የኖሩ ናቸው።

ኮሎኔል ጎሹ ምንም እንኳን የደርግ አባል በኃላም አፈንጋጭ የፓለቲካ ስደተኛ ቢሆኑም የደርግ መንግስት በብዙዎች ዘንድ የሚደነቅበትን

«የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን እና ሉአላዊነትን አሳልፎ ያለመስጠት» ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አራማጅ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያን የፓለቲካ ታሪክ የሚያወቅ ያውቀዋል።

ኢህአዴግ ደርግን ጥሎ ወደ ስልጣን በመጣበት ማግስት ከተከሰቱ ግዙፍ ሀገራዊ ጉዳዬች መካከል የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል ነበር።

ኮሎኔል ጎሹ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሰሙ ፓለቲከኛ ናቸው።

ጉዳዮን አስመልክቶ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኤርትራ መገንጠል ምክንያት የሆነውን የህዝበ-ውሳኔ (ሪፈረንደም) መደገፍን በምሬት የተቹበት ንግግራቸው ኮሎኔል ጎሹ በታሪክ የሚወሱበትን ክስተት ፈጥሮ አልፏል።

ኮሎኔሉ በኤርትራ መገንጠልን የተመለከተ ስብሰባ ላይ በወቅቱ ሀገር የተቆጣጠረው ኢህአዴግን እውቅና በመንፈግ ኢትዮጵያ ያልተወከለችበት ነገር ግን ስለ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚወሰንበት የሴራ መድረክ መሆኑን መረር አድርገው ገልፀዋል።

ኮሎኔል ጎሹ የአለማቀፍ ማህበረሰብ በአጠቃላይ አሜሪካ ደግሞ በተለይ «ኢትዮጵያን ሀገር ቀርቶ ቤተሰብ መምራት ለማይችሉ የወንበዴ ቡድኖች አሳልፈው ሰተዋል» ሲሉ ከሰዋል።

የኤርትራ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ ይወስን የሚለውን አካሄድም ኮሎኔል ጎሹ ሦስት ምክንያቶች ጠቅሰው ትክክል እንዳልሆነ ሞግተዋል።

እንደ ኮሎኔል ጎሹ ከሆነ የኤርትራ ህዝብ በሀይለ ስላሴ ዘመን በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሀድ የወሰነ በመሆኑ ሀገራችን በየሀምሳ አመት ህዝበ-ውሳኔ የምታካሂድበት አግባብ ያለመኖሩን ጠቅሰው ተከራክረዋል።

የኮሎኔል ጎሹ ሁለተኛ መከራከሪያ ደግሞ የኤርትራን ጉዳይ መወሰን ያለበት በህዝበ ውሳኔ ከሆነ የኤርትራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሳተፍ መደረግ አለበት የሚል ነበር።

ሦስተኛ የኮሎኔል ጎሹ መከራከሪያ ደግሞ የኤርትራን መገንጠል ያመጣው ህዝበ ውሳኔ የሚካሄደው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሌለበት እና

ኤርትራ ኮሎኔል ጎሹ አምባ ገነን እስታሊናዊ ፓርቲ ባሉት ሻበዕቢያ ቁጥጥር ስር ስለነበረች ውሳኔው ዲሞክራሲያዊና ፍትሀዊ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ በመግለፅ ነው።

ምንም እንኳን የኮሎኔሉ ፍላጎት ሳይሳካ የቀረ ቢሆንም ይህ ንግግራቸው በታሪክ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከተደረጉ ወሳኝ ንግግሮች ተርታ ተሰልፎ ይገኛል።

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በደርግ ዘመን ለአስራ ሁለት አመታት በወሳኝ የስልጣን እርከኖች ላይ የነበሩ ሲሆን እሳቸው ያመኑበት አብዬታዊ መንግስት አምባገነን ሰው በላ እየሆነ በመምጣቱ አሜሪካ ለስራ በሄዱበት ስርዓቱን ከድተው በዛው መቅረታቸው ይታወቃል።

ኮሎኔሉ በዛው ለመቅረት በወሰኑ ጊዜ አከናወኑት የተባለው ተግባር የስነምግባር ምጥቀታቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነበር።

ኮሎኔል ጎሹ ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ሲቀሩ የተሳጣቸውን ለመመለሻ ትኬት የሚሆን ለጊዜው መጠኑን የማላስታውሰው ዶላር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አሜሪካ በሚገኝ ባንክ አማካኝነት እንደላኩ የሚነገረው ተግባራቸውን ሳስብ እና

መለስ ብዬ ዘንድሮ በመንግስ ወጪ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሰው ሆቴል ተይዞላቸው ሀገር የሚያሳድግ ተግባር ውስጥ ከመግባት ይልቅ ሰዎችን ማበጣበጥ የያዙትን ፓለቲከኞቻችንን ሳይ ፓለቲካችን ከበፊት ጀምሮ የተበላሸ ቢሆንም አሁን ደግሞ የባሰ እንደ ዘቀጠ ያሳየኛል።

ከኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ስርዓቱን ከድቶ ከሀገር መውጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ድንቅ ነገር ደግሞ በወቅቱ ለነበሩት የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለ ማርያም የላኩት ደብዳቤ ነበር።

ደብዳቤውን ካነበብኩት ብዙ አመት የሆነኝ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ አላስታውስም (በዚህ አጋጣሚ ያለው ቢያጋራኝ ደስ ይለኛል።) የደብዳቤያቸውን ሙሉ ጭብጥ ግን የሚረሳኝ አይደለም።

ኮሎኔል ጎሹ በደብዳቢያቸው ላይ የደርግ ስርዓት በጥሩ ሁናቴ የተጀመረውን አብዬት በኃላ ባሳደገው አምባገነናዊ ባህሪ ምክንያት ገደል እንደከተታቸው ፅፈዋል።

አያይዘውም እሳቸው ይህን ችግር ከውስጥ ለመፍታት ያደረጉት ጥረት መንግስት ውስጥ ባሉ አድር ባዬችና አጋጣሚ ጠባቂዎች ምክንያት ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ፅፈዋል።

በአሁኑ ስዓት ምናልባት ሊገርም የሚችል ነገር ቢኖር ደብዳቤቸው ውስጥ የለውጥ ጠንቅ የደርግ ሰዎችን ኮሎኔል ጎሹ «የፓለቲካ ጅቦች» ያሏቸው መሆኑ ነው። (የዛኔው የቀን ጅብ ¡?)

በማጠቃለያዬ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን የኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ደብዳቤ ውስጥ የደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ፓለቲካ ችግሮችን የቃኙበት መንገድ አሁንም እንኳን ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮቻችንን የሚያሳይ መሆኑን ነው።

ለማንኛውም ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ድንቅ ፓለቲከኛ እና ምሁር የሆኑት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው የተሰማኝን ደስታ መግለፅ እወዳለሁ።

የመሠረተ ትምህርት ዘመቻችን ጠቅላይ አዝማች! ኢትዮጵያ በስኬታማው የ1970ዎቹ ዘመቻ በዩኔስኮ ስትሸለም ፊታውራሪው ዶር. ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ነበሩ።

የመዠመርያው የገጠር መሠረተ ትምህርት ዘመቻ በ3ኛው ዙር ዘመቻ ጎንደርና ሐረር ለመዝመት ሚያዝያ 23 ቀን 1972 ዓ.ም. በሜይዴይ በዓል በአብዮት አደባባይ እኛ አዲሳባውያን ስንከት በርእስ ብሔሩ በሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም ፊት ተሰልፈን ያለፍነው በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር ጎሹ ወልዴ መሪነት ነበር።

ከመንፈቅ በኋላ ወደ መናገሻ ከተማችን በጥቅምት መባቻ በተመለስን በሳኒታው በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ ሞቅ ያለ አቀባበል ያደረጉልንም እሳቸው ናቸው። እንኳን ደህና መጡ!!!!

በነገራችን ላይ የመትዘ/ ዘመቻው በሐምሌ 1971 ዓ.ም. ሲጀመር እነ ፀሓይ ዮሐንስ ”ማንበብና መጻፍን…” ሲያቀነቅኑ ዘመቻው ሲቀጣጠል ሚኒስትሩ የመስክ ጉብኝት ይወጡ ነበር።

በሐምሌ መገባደጃ ይመስለኛል አዲሳባችን ካዛንቺስ ልዕልት ዘነበወርቅ(ፒዜድ)/ በኋላ የካቲት 6 አሁን ሚስስ ፎርድ ትምህርት ቤት ከሚገኘው የከፍተኛ 15 ቀበሌ 28 (09- 04-28)የመሠረተ ትምህርት ጣቢያ ኮሎኔል ጎሹ ለቅኝት ሲመጡ መጀመርያ ጎራ ያሉት እኔና አሰለፈች ናደው ከምናስተምርበት ክፍል ነበር።

ለሚማሩት ጎልማሶች፣ እናትና አባቶች ማትጊያ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከመውጣታቸው በፊት ወደ አንድ አረጋዊ ቀረብ ብለው ስሜታቸውን ጠየቋቸው።

“መማሬ ባይከፋም ከሽምግልናዬ ጋር ግን አልሆነልኝም፤ ተገድጄ ነው ምመጣው” ሲሉ ጓድ ጎሹም ” ካልፈለጉ አሁኑኑ ወደቤትዎ መሔድ ይችላሉ” ሲሉ መርቀው እጅ ስመው ወደ ቀያቸው ማምራታቸውን አስታውሳለሁ።

የፎቶ መግለጫ: የዘመቻ ሸሚዛችን ኪስና የዘመትኩበት አውራጃ በቀድሞው አጠራር በጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቦ አውራጃ ያሳተመው የፊደል ገበታ።

ወረዳው ከምከም ቃሮዳ ከተማው አዲስ ዘመን ቀበሌው ” ስልቂሳ ሁልጊዜ ወደፊት ቀበሌ ገበሬ ማኅበር” ይባል ነበር።

አሳዳሪያችን አያ ሙጬ ጌታሁን ክብርት ባለቤታቸው እመት ሥራው ድንቅ አዳነ፣ ልጃቸው አስማረ ሙጬ፣ ጎረቤታቸው አዜ በየነ ታወሱኝ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here