የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኬንያ የመልስ ጨዋታ 3 ለ0 በሆነ ሰፊ ልዩነት ተጠናቀቀ።

ወደ ኬንያ ናውሮቢ በማምራት ከኬንያ ብሃራዊ ቡድን ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3ለ0 በሆነ ሰፊ ልዩነት ተረትቷል።

በመጀመሪያው 45 ደቂቃ የጨዋታ አጋማሽ በ2 ለ0 ሲመራ የቆየው ብየራዊ ቡድኑ ያለምንም ግብ ወደ ሁለተኛው የጨዋታ አጋመሽ የተሸጋገር ሲሆን፥

የኬንያ ብሄራዊ ቡድን በ2ኛው የጨዋታ አጋማሽ 66ኛ ደቂቃ ላይ ያገኛትን ፍጹም ቅጣት ወደ ጎል በመቀየር 3ኛ ግቡን አስቆጥሯል።

በዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያለ ምንም ግብ የጨዋታውን መደበኛ ጊዜ እና ተጨማሪ 3 ደቂቃዎችን ሲያሳልፍ የኬንያ አቻው 3 ጎሎችን በማስቆጠር ድል ቀንቶታል።

በሳላፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የኬንያ አቻው በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲያም ተገናኝተው ባዶ ለባዶ መለያየታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ስድስት ከጋና፣ ከኬንያ እና ከሴራልዮን ብሄራዊ ቡድኖች ጋር የተደለደለ ሲሆን፥

ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አክራ ላይ በጋና አቻው ሲሸነፍ በሀዋሳ ስታዲየም ደግሞ ሴራሊዮንን አሸንፏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here