• ዓርብ የካቲት 12/1929 ዓ.ም ማለዳ፤ እምቢ ባዩ አብረሐ ደቦጭ ከቤቱ ሲወጣ የኢጣልያን ሰንደቅ ዓላማ የቤቱ ወለል ላይ ዘርግቶ “ከእንግዲህ በቃኸኝ” በሚል ስሜት ጦር ሰክቶበት ተራምዶት አለፈ፡፡

• የጣሊያን ቋንቋን አቀላጥፎ መናገር በመቻሉ በአዲስ አበባው የፋሺስት ፖለቲካ ቢሮ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው አብረሐ ደቦጭና ጓደኛው ሞገስ አስገዶም በፋሺስቶች ድግስ ላይ ታሪክ ለመስራት መዘጋጀት ጀምረው ነበር፡፡

• ይህ ቀን ከመድረሱ በፊት ሁለቱ ወጣቶች የእጅ ቦምቦችና ፈንጂዎችን በማዘጋጀት ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ወደ ሚገኘው ዝቋላ ተራራ በመሄድ እንዴት ጥቃት ማድረስ እንደሚችሉ ልምምድዶችን አካሂደዋል፡፡

• በ19ኛው ክ/ዘመን ማጠናቀቅያ ላይ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ሞክሮ ያልተሳካለት የኢጣልያ መንግስት በ1927 ዓ.ም ዳግም የወረራ ውጥንን በመያዝ ወደ ሀገራችን መጣ፡፡

• ሀገሪቱን በተቆጣጠረ በ2ኛ ዓመት ገደማ፤ ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒ በጣሊያን ንጉሣዊ ቤተሰብ ልዑል ኒፕልስ የተባለ አዲስ ህፃን መወለዱን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ ደማቅ ክብረ-በዓል ማዘጋጀት አቀደ፡፡

• የካቲት 12/1929 ዓ.ም በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ (የቀድሞ ገነተ-ልዑል ቤተ መንግስት/የአሁኑ ሙዝየም) ደጃፍ በርካታ ነዋሪዎችን አሰባሰበ፡፡

• ዕለቱ ደርሶ ዝግጅቱም እዲካሄድ ታውጆ ህዝቡ በቤተመንግስቱ ደጃፍ በተሰባሰበባት ዓርብ ማለዳ፤ ያዘጋጇቸውን መሣርያዎች እንደያዙ ለጥቃት ይመቻቸው ዘንድ በህዝቡ መሃል በማለፍ ግራዚያኒ ንግግር ከሚያደርግበት መነጋገርያ አቅራቢያ ተገኙ፡፡ እንደ ዝግጅቱ አድማቂ በመቆጠራቸውም ጥርጣሬ ያሳደረባቸውም ሆነ እንዳይጠጉ የከለከላቸው ፋሺስት አልነበረም፡፡

• አብረሐ ህዝቡን ከጉዳት ለማዳን ግራዚያኒ ንግግር ወደ ሚያደርግበት ብዙም እንዳይጠጉ የነገራቸው ነዋሪዎች፤ አብረሐ በፋሺስት ቢሮ ይሰራ ስለነበረ ሊያምኑትና ማስጠንቀቅያውን ሊቀበሉት አልፈቀዱም ነበር፡፡

• ዕኩለ-ቀን ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወጣቶቹ ጥቃታቸውን ፈፀሙ፤ የያዟቸውን ቦምቦች ወረወሩ፡፡

• ሩዶልፎ ግራዚያኒን፣ ምክትሉ አርማንዶ ፔትሬቲና የአየር ኃይል መሪያቸውን ጄኔራል ሊዮታ (አንድ እግሩ አጥቷል) ጨምሮ ሰላሳ የሚጠጉ የፋሺስት መሪዎችና አጃቢዎች ቆሰሉ፡፡

• የጣሊያን የመልስ እርምጃ እጅግ የፈጠነ ነበር፡፡ በዚያው ዕለት ምሽት ህዝቡ እንዲሰባሰብና እርዳታ እንዲቀበል ጥሪ ካደረጉ በኋላ በተሰባሰበበት አይናቸውን ጨፍነው ይጨፈጭፉት ጀመር፡፡

• በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት፤ ቅዳሜና ዕሁድም. . .

• በአየርና በምድር ንፁህ ኢትዮጵያውያን ተረሸኑ፡፡

• በየቤታቸው ያሉትንም ጋዝ አርከፍክፈው ያቃጥሏቸው ገቡ፡፡

• በግሪኮች በኢንግሊዛውያንና ሌሎች የአውሮፓ ዜጎች ቤቶች ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩትም ከየቤቱ እየተገፉ ተረሸኑ፡፡

• ሰላሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገደሉ፤

• /ክብር ለየካቲት 12 ሠማዕታት/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here