ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግብዣ የመሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያይ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ቆይታ እንደሚያደርጉም የገለጸው ጽህፈት ቤቱ፥ ህዝቡ በደማቅ ኢትዮጵያዊ አቀባበል ኤርትራውን ፕሬዝዳንት እንዲቀበል ጥሪ አቅርቧል።

በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

በተጨማሪም ወደ ሀዋሳ ከተማ በማቅናት የሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚታደሙበት መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ መዘጋጀቱንም ለማወቅ ችለናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ካሳለፍነው እሁድ ሀምሌ 1 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኤርትራ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አስመራ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የአስመራ ከተማ ነዋሪ ኤርትራውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ የሰላም እና የወዳጅነት ስምምነት መፈራማቸውም ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ሁለቱ ሃገራት በድንበር ሳቢያ ግጭት ከገቡ በኋላ አስመራን የረገጡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሪ ሆነዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here