ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ለማጠናከር ከኤርትራ የእግር ኳስ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ

አስመራ ከተማ ላይ ለማድረግ ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የላክነው ታሪካዊ ደብዳቤ ታሪካዊ ምላሽ

አግኝቷል፡፡

የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቁጥር ENFF 9/342/18 በቀን 12/7/18 G.C

በአማራ ክልላዊ መንግስት በጎንደር ከተማ አስተዳደር ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በተፃፈ ደብዳቤ ጥያቄውን መቀበላቸውን በአድናቆት ምላሽ ልከዋል፡፡

የኤርትራ እግርኳስ ፌዴሬሽን በላከው ታሪካዊ ደብዳቤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ሰላምና ፍቅር አብሮነት ለማጎልበት በሁለቱ ሀገራት መካከል የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ ትልቅ ተግባር እንደሆነ በመግለፅ ክለቡንም እንደሚያደንቁ ገልፀዋል፡፡

የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅድመ ዝግጅቶችን በቅርብ ቀናት በማጠናቀቅ ጨዋታው ታሪካዊ ሁኖ አስመራ ከተማ ላይ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ደስታቸውንም አበክረው ገልፀዋል፡፡

የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፋሲል ከነማ በኤርትራ ፕሪምየርሊግ ውስጥ ከሚጫወት የእግር ኳስ ክለግ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀበለ።

ፌዴሬሽኑ በፃፈው የመልስ ደብዳቤም የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ለመጫወት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቋል።

የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአስመራ ላይ በቅርቡ ለማካሄድ የተሰበውን የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ መጀመሩንም አስታውቋል።

የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታው የሚካሄድበት ቀንም በቅርቡ እንደሚያስታውቅ ነው ፌዴሬሽኑ ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በላከው ደብዳቤ ያስታወቀው።

የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ያቀረበው የወዳጅነት የእግር ኳስ ጥያቄም የሀገራቱ መሪዎች ሰላምን ለማስፈን የጀመሩትን ስራ የሚያጠናክር ነው ሲልም አድንቆታል።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ከሚጫወት ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሰኔ 30 2010 ዓ.ም ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here