ኘሮፌሰር መስፍን የወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ በኘሬዝደንትነት መመረጥ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ:-

~ ወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ ለሶስት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዞችን (በእኔ ግምት አፄ ኃይለስላሴ፣ ደርግ እና ኢህአዴግ) በታማኝነት ያገለገለች ነች፣

ይህን አስተዋፅኦ ከባድ ሚዛን ውስጥ ገብቶ የኢትዮጵያ መሪ እንድትሆን ተመርጣለች።

የእኔ ዋናው ነገር የወ/ሮ ሣህለወርቅ መመረጥ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እልል ብሎ መቀበሉ ነው።

ይህ ከታሪኩ የማይማር መሆኑን በግልጵ ያሳያል ሲሉ ሕዝቡን ጭምር ሸንቆጥ አድርገዋል።

#የእኔ ጥያቄ ለኘሮፌሰሩ – ፍሬው አበበ አደራ

~ ሶስት አገዛዞችን በሙያው ያገለገለ ኢትዮጵያዊ በጅምላ እንደበዳይ፣ እንደአጥፊ አድርገው ለምን ሊፈርጁ ቻሉ?

በአገዛዞች ውስጥ ቁልፍ ስልጣን ሁሉ ይዘው አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት ያገለገሉ አልነበሩምን? ከእዚህስ አንዷ ወ/ሮ ሣህለወርቅ አይደሉምን?

~ በዚህ አስተሳሰብ መሰረት ኘሮፌሰሩም ቢያንስ ሁለቱን አገዛዞች በሙያቸው ስላገለገሉ የገዥው መደብ አካል ወይንም ፀረ ሕዝብ ነበሩ ማለት ነውን?

~ በኢህአዴግ ዘመን ሶስቱን አገዛዝ ያገለገለ ሰው መሾሙ አዲስ ነገር ነውን? በዚሁ ቦታ የመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሲሾሙ ኘሮፌሰሩ ምነው ድምፃቸውን ሳያሰሙ ኖሩ? ወይንስ ያኔ ይህ ነገር አልተገለጠላቸውም?

#በመጨረሻም
በደፈናው “ወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘውዴን ሶስት አገዛዞችን አገልግለዋል፣ ሕዝቡ ለምን ድጋፉን ሰጠ” በሚል ስማቸውን ለማጠልሸት ኘሮፌሰሩ የመመዘዙት ብዕር እንኳንስ ሌላውን ቀርቶ ራሳቸውን ማሳመን የማይችል፤ ከተራ ቅናትና ምቀኝነት የተነሳ መሆኑ አሳዝኖኛል።

***

#ዮሐንስ ሞላ እንዲህ አለ … #Yohanes Molla

አይ ፕሮፌሰር!

ከልጅነት ዕድሜው አንስቶ ኢህአዴግን በታማኝነት እና ቁርጠኝነት ሲያገለግል ለኖረው፣ ሿሚው አብይ እልል በሉ
እያሉ
ለተሿሚዋ ወ/ሮ ሣህለወርቅ ሹመት እልል አትበሉ ይላሉ?! 🤔

(አጭሬ። እዚሁ የተሰነኘ።
ኢንስፓየርድ ባይ Yonas A Chekol)

“ከናንተ ሀጥያት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት።” ~ ዮሐንስ 8:7

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here