የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ7 ሺህ 611 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

ይቅርታ ከተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች ውስጥ 7 ሺህ 183 ወንዶች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ 428 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

ለህግ ታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረጉት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ፥ በክልሉ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም ላይ ለ6 ሺህ 655 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ ይታወሳል።

እንዲሁም በታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ለ10 ሺህ እና በሰኔ ወር 2009 ዓ.ም ላይ ደግሞ ለ6 ሺህ 430 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here