አብዛኛወቻችሁ ይህን ቀን በደንብ ታስታውሱታላችሁ ግን ጊዜው በጣም እየራቀ ስለመጣ እድሜያችሁ እንዲታወቅ ስለማትፈልጉ ይህንን ታሪካዊ ቀን በተመለከተ አስተያየት እንደማትሰጡኝ ርግጠኛ ነኝ።

የእኛ ሰው ከሞት የበለጠ እድሜ ይፈራል። ሁሌም ልጅ፣ ኮረዳ ፣ ጎረምሳ፣ እንደተባለ ለመኖር የሚመኝ የዋህ ህዝብ ነው።

ከአመት ወደ አመት ሴቱ 25 ወንዱ 29 ነኝ እያለ ሲፎግር ይደመጣል።

ቦቅቧቃ ማለት ትርጉሙ ይሄ ነው። ነገር ግን በእናንተ መደበቅ ምክንያት ታሪካችንም አብሮ መደብቁ ያሳዝነኛል።

ሆኖም ይህ ታሪካዊ ቀን በግድም ሆነ በውድ መታወስ አለበት።

የቆሙበት አላማ ምንም ይሁን ነገር ግን በታሪክ ፊት ህይወታቸውን ያስረከቡት ጄኔራሎች በሙሉ መታወሰ አለባቸው ብዬ ስለማምን ከዚህ በፊት የለጠፍኩትን የማስተወሻ ታሪካቸውን በድጋሚ ሼር አደርገዋለሁ።

በወቅቱ የተለያዩ ሰወች የሰጡትን አስተያየት አንብባችሁ የተለጠፉትን ፎቶወቹን አይታችሁ ይህን ቀን ከእኔ ጋር አብራችሁ አስታውሱት።

በዚህ የእራት ግብዣ ምስል ላይ የሚታዩት መፈንቀለ መንግስቱ ከከሸፈ በኃላ ራሳቸውን ያጠፉት ጄኔራል አማሃ ደስታ እና ጄኔራል ንጉሴ ዘርጋው ናቸው።

እንዲሁም ሜ/ጄ ሃይሉ ገ/ሚካዔል፣ ሜ/ጄ ወርቁ ዘውዴ ፣ ሜ/ጄ አለማየሁ ደስታ ፣ሜ/ጄ ዘውዴ ገብረየስ ፣ጄኔራል ሰለሞን በጋሻው ፣ ብ/ጄ እንግዳ ወ/ አምላክ ፣ብ/ጄ ነጋሽ ወልደየስ ፣ብ/ጄ እርቅይሁን ባይሳ ፣ብ/ጄ ተስፋዬ ትርፊ ተሳትፈው ሰለባ ሆነዋል

በተጨማሪም ጄኔራል መርዕድ ንጉሴ ፣ ጄኔራል ፋንታ በላይ ፣ጄኔራል ደምሴ ቡልቱ ፤ወዘተ በመፈንቅሉ መሪነት ህይወታቸውን ለግሰዋል ።

ጄኔራል ቁምላቸው ደጀኔ ከአገር ሸሽተው አምልጠዋል እነዚህ ጄኔራሎች እንዲታወሱ ለሌሎች ሼር በማድረግ ተባበሩኝ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here