የኩባው ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በመጋቢት ወር 2018 ስልጣን እንደሚለቁ ተነግሯል።

ካስትሮ ስልጣን እንደሚለቁ የታወቀው የእሳቸውን ስፍራ የሚተካ ሰው በትናነትናው እለት የሀገሪሩ ብሄራዊ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚመረጥበትን ቀን በመቁረጡ ነው።

ውሳኔውም የ86 ዓመቱ ራውል ካስትሮ ስልጣን ይለቃሉ ተብሎ የነበረው ጊዜ ላይ የሁለት ወራት ተጨማሪ ጊዜን የሚሰጥ ነው ተብሏል።

HAVANA (Reuters) – Cuban President Raul Castro announced on Sunday he will step down from power after his second term ends in 2018, and the new parliament named a 52-year-old rising star to become his first vice president and most visible successor.

የሀገሪቱ ብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ፥ “ሁለተኛው እና የመጨረሻው የስልጣን ዘመኔ የፊታችን መጋሚት ወር ይጠናቀቃል፤ ኩባም አዲስ ፕሬዚዳንት ይኖራታል” ብለዋል።

የፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮን ስፍራም ምክትላቸው የ57 ዓመቱ ሚጌል ዲያዝ ካኔል እንደሚረከቡም ተገምቷል።

የፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ የስልጣን ቆይታ በጥር ወር ነበር ያበቃል የተባለው፤ ሆኖም ግን ሀገሪቱ ላይ በከፍተኛ አውሎ ንፋስ አደጋ በደረሰ ጉዳት በመስከረም ወር ላይ ሊካሄድ የነበረው ምርጫ በመገፋቱ ነው ለተጨማሪ ሁለት ወራት ሰልጣን ላይ የቆዩት።

ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ወንድማቸው ፊደል ካስትሮን በመተካት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት።

የፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ ሰልጣን መልቀቅም ላለፉት 60 ዓመታት ሀገሪቱን በመምራት ላይ የነበረው የካስትሮ ቤተስብ አመራር ፍፃሜ ይሆናል ተብሏል።

“This will be my last term,” Castro, 81, said shortly after the National Assembly elected him to a second five-year tenure.

In a surprise move, the new parliament also named Miguel Diaz-Canel as first vice president, meaning he would take over if Castro cannot serve his full term.

ራውል ካስትሮ ወንድም ፊደል ካስትሮ ሀገሪቱን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1959 አንስቶ እስከ ህልፈተ ሀይወታቸው ድረስ ሀገሪቱን መምራታቸው ይታወሳል።

የኩባ የነፃነት አባት በመባል የሚጠሩት እና በሀገሪቱ ህዝብ ዘነድ ከፍተኛ ፈቅር እና ተቀባይነት የነበራቸው ፊደል ካስትሮ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here