የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ቡድን መሪ የነበሩቱ አቶ ማሩ ገብረፃዲቅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚያካሂዳቸው ማንኛውም ውድድሮች የእድሜ ልክ እገዳ ተጣለባቸው።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደበት ወቅት መከላከያ ሁለተኛን ጎል በ84ኛው ደቂቃ ማስቆጠሩን ተከትሎ የቡድን መሪ የሆኑት አቶ ማሩ ገብረፃዲቅ በመሀል ዳኛው በፌደራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ላይ ድብደባ መፈፅማቸው ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪ የዲስፕሊን ኮሚቴው የወልዋሎ ተጫዋቾች በረከት አማረ፣ አለምነህ ግርማ፣ አስሪ አልማህዲ፣ ማናየ ፋንቱ፣ በረከት ተሰማ እና አፈወርቅ ኃይሉ ለስድስት ወራት እንዲታገዱ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ብር 10 ሺህ ቅጣት እንዲከፍሉ እንደተወሰነባቸው ተነግሯል።

ሌላው የወልዋሎ ተጫዋች ዋለልኝ ገብሬ የሁለት ዓመት እገዳ እና የ15ሺህ ብር ቅጣት እንደተላለፈበት የተገለፀ ሲሆን፥ ወልዋሎ በጨዋታው የፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆንና 250 ሺህ ብር እንዲከፍል እንደተወሰነበት ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሶኮር ኢትዮጵያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here