የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በተመድ ከአሜሪካ አምባሳደር ከሆኑት ኒኪ ሃሊ ጋር በዋሽንግተን ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት በመንግስት የተጀመረው የፓለቲካ ምህዳር የማስፋት እንቅስቃሴ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

መንግስት የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አገሪቱ ጠንካራና የተሻለ ለማድረግ ክፍለ አህጉራዊ ሚናዋን እንደምትወጣም ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደቱን የማሳለጥ እንቅስቃሴ እንዲሳካም ኢትዮጵያ በኢጋድ ጥላ ስር የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች::

አምባሳደር ኒኪ ሃሊ በበኩላቸው የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት እያካሄደ ያለውን ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ በጽኑ ይደግፋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ የሰላም ሂደት እንዲሳካ በኢትዮጵያ የሚደረገውን ጥረት አመስግነው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ለምታደርገው እንቅስቃሴ አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋር ሁና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here