በደቡብ ክልል የኮንሶ ባህላዊ መሪ  ካላ ገዛህኝ ወልደዳዊትን ጨምሮ የ188 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሪት ትዛታ ፈቃዱ፥ ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሰዎች በክልሉ በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን

በኮንሶ ወረዳ ከ2007 እስከ መስከረም 2009 በነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ናቸው ብለዋል።

በሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር የቆዩት ግለሰቦቹ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነው

የተሻለ አገራዊ መግባባትን በመፍጠር የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትእንዲሁም

አሁን በአገራችን የጀመርነውን የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመደመር፣

የአንድነትና እንደ አገር የመለወጥ ጉዞ እውን ለማድረግና ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ነው።

ቢሮው እንዳስታወቀው ከፌዴራል አቃቢ ህግ በተሰጠው ውክልና መሰረት ሰው በመግደል በከባድ ወንጀል ከተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች ውጭ

በስምንት መዝገቦች ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ 188 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

እነዚህ ክሳቸው የተቋረጠላቸው ግለሰቦችም ሰላም በአመፅና በሁከት እንደማይገኝ በመገንዘብ እና

ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ጥላቻን በፍቅር በመተካት ለውጥ ለማምጣት ሊሰሩ እንደሚገባ ክልሉ አሳስቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here