የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣

እንደጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ።

አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፍ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው ላይ እንደገለፁት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ቀን 1434 ዓ.ም ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለ20 አመታት በእስር ኖረዋል።

ሆኖምግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ።

በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እየተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣

በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ የሚፈራበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር።

የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅምን አልተረዳውም ነበር።

ይልቁኑ ፊትለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጡ።

ዓፄ ዘርአያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ።

በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤ/ክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲቀጥል ቆይቶ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት)፣

የግብጽ ጳጳሳት በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል።

በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀቃቸው ግዛታቸው ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር።

በ1446 ዓ.ም የሀሌይ ኮሜት (ባለጭራ ኮኮብ) ደማቅ ብርሃኑዋን እያፈናጠቀች ስታልፍ፣

አጼው የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል።

እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።

ANRS Debre Birhan city Communication Affairs Office

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here