ሦስቱም – የተገደሉበት ሥፍራ ከሙገር አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ፣ የቻይና ስሚንቶ ፋብሪካን አልፎ ዳገት እና ጫካ ካለበት ሥፍራ ነው፡፡

ሟቾቹ – የዳንጎቴ ስሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ህንዳዊው ዲፕ ካማራ እና ሁለቱን ኢትዮጵያዊ ሠራተኞች ማለትም ጸሐፊውንና የሦስት ልጆች እናት ወ/ሮ በአካል አለልኝ እንዲሁም ሾፌሩን  ናቸው፡፡

ፊታቸውን የተሸፋፈኑ ሰዎች ተኩሰው በመግደል ወደ ጫካ እንደገቡ የዓይን እማኞች ጠቅሶ የፋብሪካው ሠራተኛ ተናግሯል፡፡

መጀመሪያ የሾፌሩን አንገት እንደተመታ እና ጥቂት ተጉዞ መኪናው እንደተጋጨ እነዲሁም ዲፒ ካማራ በር ከፍቶ ለማምለጥ እግሮቹ መሬት እንደረገጡ ብዛት ባለው ጥይት እንዲሁም የሦስት ልጆች እናት በሦስት ጥይቶች ደረቷና ጎኗን መመታቷን ተናገረዋል፡፡

የሟች ወ/ሮ በአካል አለልኝ ሥርዓተ-ቀብር ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው አቦ ቤተክርስቲያን የተፈጸመ ሲሆን ሲሆን መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው የፀጋይ ጊደይ አስከሬን ወደ ትግራይ ዓዲግራት ከተማ ተሸኝቷል፡፡

ፀጋይ ጊደይ ባለትዳር ነበር፡፡ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የሚሰራው ታላቅ ወንድሙ የወንድሙን አስከሬን ይዞ ለሊት ዓዲ ግራት ገብቷል፡፡

የህንዳዊው ዲፕ ካማራ አስከሬንም ትናንት ምሽት 2፡30 ላይ ወደ ህንድ ተሸኝቷል

ነፍስ ይማር!!!

በነገራችን ላይ …

ናይጄሪያዊው ቢሊየነር ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንትቸውን በእጥፍ ሊያሳድጉ መሆኑን አምና በጥር ወር አስታውቀው ነበር

ከሁለት አመት በፊት በፋብሪካቸው ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል መሆኑን በመጥቀስ አገሪቷን የኢንቨስትመንት ምርጫቸው ከማድረግ እንደማያግዳቸው ይልቁንም መዋዕለ ነዋያቸውን በቅርቡ በእጥፍ እንደሚያሳድጉ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ባለቤት ናይጄሪያዊው ቢሊኒየር አሊኮ ዳንጎቴ ተናግረዋል።

ባለሀብቱ ከቀድሞ ኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ገበያ በማስፋፋት ዙሪያ በሰፊው ተወያይተዋል።

ከውይይት በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ባለሀብቱ፤ “አሁን ላይ እያማተርን ያለነው የኢንቨስትመንት ፍሰታችንን በእጥፍ ማሳደግ በምንችልበት ጉዳይ ላይ ነው።

በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት የሲሚንቶ ቀረጢቶችን ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ እንገነባለን። ምርታችንንም አሁን ካለው በእጥፍ ለማሳደግ አቅደናል።

አያይዘውም ባለሃብቱ ዳንጎቴ

“ከሲሚንቶ ውጭ በሌሎችም ኢንዱስትሪዎች የመሰማራት ፍላጎት አለን። በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመርኩትን የኢንቨስትመንት ትስስር አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

ውይይቱን የተከታተተሉት በቀድሞ ሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዴሊቨሪ ዩኒት ሃለፊ አቶ ዛዲግ አብረሃ ባለሀብቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ምቹ በሆነ ሁኔታ ኢንቨስትንታቸውን እንዲያስፋፉ መንግስት ማድረግ ስሰልሚችለው ነገር አብራርተውላቸዋል።

“ዳንጎቴ ሲሚንቶ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የተወሰነ ችግር አጋጥሞ ነበር። የተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲያ ይሄንን አጋነው በማቅረብ ኩባንያው ከኢትዮጵያ የመውጣት ሃሳብ እንዳለው ሲያስተጋቡ ነበር።

ባለሀብቱ ግን አይደለም ሊወጡ ኢንቨስትመንታቸውን አጠናክረው በእጥፍ ለማሳደግ ወስነዋል” ሲሉም ነበር በወቅቱ አቶ ዛዲግ የገለጹት።

በሌሎች የአፍሪካ አገራት ካሉ ፋብሪካዎቻቸው እዚህ ያለው አትራፊ እንደሆነ ባለሀብቱ መግለጻቸውን የጠቀሱት አቶ ዛዲግ፤ ኢትዮጵያ ሰርተው የሚከብሩባት አገራ መሆኗንም መስክረዋል ብለዋል።

ዳንጎቴ ሲሚንቶ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በ600 ሚሊዮን ዶላር የሚካሄድ ኢንቨስትመንት ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ በህንዳዊው ዲፕ ካማራ እና 2 ኢትዮጵያውያን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሰራተኞች ላይ በተፈፀመው ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ማዘናቸውንና መንግስታቸው በወንጀሉ ፈፃሚዎች ላይ በአስቸኳይ ምርመራ በማድረግ ጉዳዩን ለፍትህ እንደሚቀርቡ መናገራቸውን አቶ ፍፁም በቲውተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ቢቢሲ አማርኛ ደግሞ ከጥቃቱ በኋላ በቦታው የተገኙ የዓይን እማኞች ነገሩኝ እንዳለው ከሆነ ጥቃቱ የተሰነዘረባቸው ሰዎች ይጓዙበት በነበረው ቶዮታ ላንድክሮዘር መኪና አካባቢ 17 የሚሆኑ የጥይት ቀለሃዎችን አይተዋል ብሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በነበረው አለመረጋጋት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ላይ ጥቃት ተሰንዝሮባቸው እንደነበር ያስታወሰው የወሬ ምንጩ ሆኖም በአካባቢው ህብረተሰብና በፋብሪካው ሀላፊዎች መካከል በተደረገው ውይይት መልካም የሚባል ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ በአካባቢው ህብረተሰብም ተወዳጅ ነበሩ ያለው የወሬ ምንጩ የአደአ በርጋ የኦህዴድ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ድሪርሳ ታደሰ ስራ አስኪያጁና ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የተገደሉት ጋቲራ በተባለ ቦታ መሆኑን እንደነገሩት ፅፏል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቅሙት የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤቱ ናይጄሪያዊው ቱጃር አሌኮ ዳንጎቴ ዛሬ አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዳንጎቴ የሚመጡት ቀድሞ በያዙት ዕቅዳቸው ይሁን በድንገት መረጃዎች ያሉት ነገር የለም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here