(ጌታቸው ለማ)

በአፍሪካ ምርጫን አስመልክቶ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ከዲሞክራሲ አንፃር የተጠናከረና ስር የሰደደ አለመሆኑን ነው፡፡

የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነት እንጂ የብዙኃን ፓርቲ የሚባል ነገር ብዙም አልተለመደም፡፡

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በአህጉረ አፍሪካ የብዙኃን ፓርቲ ፖለቲካ ብቅ ማለት የጀመረው በ1990 ላይ መሆኑን በአፍሪካ የጥናት ማዕከል የተጻፈው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአፍሪካ የምርጫ ወቅት ባለድርሻ አካላት ከሚባሉት ዋነኞቹ ተዋናዮች ሥልጣን ላይ ያለው ገዢ ፓርቲ ወይንም መንግስት አልያም ሁለቱንም አደባልቀው የያዙ መንግስታት፣ የሲቪል ማህበረሰቡ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ወይንም መንግስት ከመጋረጃ ጀርባ ያደራጃቸው ታማኝ ተቃዋሚዎች መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአፍሪካ ምርጫን አስመልክተው በተካሄዱ ጥናቶች ባለፉት 15 አመታት ትልቅ መሻሻል እየታየ መጥቷል እየተባለ ነው፡፡

በ1990ዎቹ በአፍሪካ ይብዛም ይነስ በፉክክር የታጀቡ ምርጫዎች ደርዘን በሆኑ ሀገሮች ተከናውነዋል፡፡

የምርጫ ባለድርሻ አካላት የተሰኙት በምርጫው ሂደት የተሻለ ፍትሃዊ አካሄድ እንዲኖር ካደረጉ፤ ዘላቂ ለሆነ ሰላም የዲሞክራሲ መንገድን በመክፈት በኩል አስተዋፅኦቸው ገንቢ እንደሚሆን እየታመነበት መጥቷል፡፡

ለአብነትም ያህል በጋና፣ በዛምቢያ፣ በሴኔጋል እና በተለየ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካ በ1994 የተደረገው የተሳካ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሊጠናቀቁ መቻላቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ሲባል ግን በአፍሪካ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምሉዕ በኩሉሄ ወይንም ሙሉ በሙሉ ከችግሮች የፀዳ ነው ማለት አይደለም፡፡

በአፍሪካ ምርጫን በሚመለከት ዋነኛ እንቅፋት ተደርገው ከሚጠቀሱት መካከል ቁሩጩ ድሃ በሆኑ ሀገሮች ሳይቀር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ አሽን የመፍላታቸው ጉዳይ ነው፡፡

ሌላው ደግሞ በጎሳና በሃይማኖት በተከፋፈሉ ሀገሮች የሚደረግ ምርጫ ለበርካታ ሰላማዊ ዜጎች እልቂትና እስራት ምክንያት መሆኑ ነው፡፡

በቅርቡ አፍሪካዊቷ ሀገር ዚምባቡዌ የቀድሞውን አንጋፋ መሪዋን ሮበርት ሙጋቤን ጤናማ ነው በሚባል መልኩ በሌላ መሪ ኤመርሰን ምናንጋግዋ መተካቷ የሚታወስ ነው፡፡

ዚምባብዌ እንደሌሎቹ በርካታ ሀገሮች በውስጧ የሚንቀሳቀሱ 107 የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖር ራሷን ያዞሩዋት ይመስላል፡፡

ሰሞኑን የዚምባብዌ የምርጫ ኮሚሽን ይህንኑ ጉዳይ በማንሳት ሀገሪቱ ይህን ያህል የፖለቲካ ፓርቲዎች አያስፈልጓትም ባይ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ…

http://shegerfm.com/2013-05-11-16-…/2068-2018-03-14-12-11-41

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here