አሁን – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዝግ ስብሰባ የፕሬዚደንት እጩ  ማድረግ ጀምሯል

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሥልጣን ርክክብ ይፈጸማል

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን እያካሄደ ነው።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥

ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ያቀርቡትን መልቀቂያ ተቀብሏል፤

በዚህ መሰረት አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት። ለአምስት ዓመታት ሰርተዋል፡፡

ሦስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዛሬ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ሥልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

***

ከቻይናው ፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ እስከ ሐርቫርድ….ህግ፣ ፖለቲካል ሳይንስ፣ ኢኮኖሚክስ እና ዲፕሎማሲ አጥንተዋል።

ከአሁኑ የቻይናው ጠሚር ጋር አንድ ባች ተማሪዎች ነበሩ። መንደሪን ቋንቋ ልክ የቻይናወቹን ያህል ያውቁታል።

– በ35 ዓመታቸው ኢትዮጵያን ወክለው በጃፓን እና አውስትራሊያን ጨምሮ በአካባቢው አገራት.. አምባሳዶር ሆነዋል።

– ምስ/ወለጋ አርጆ የተወለዱት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ሚር ድኤታ ፣ አፈ ጉባኤ (ፌ/ም/ቤት) ፣ ግብርና ሚር…ሆነው ሠርተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here