ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚካሄደው ተወዳጁ የፊፋ አለም ዋንጫ በሩሲያ አስተናጋጅነት የዛሬ ሳምንት ሀሙስ አዘጋጅ ሀገር ሩሲያ ከ ሳውዲ አረቢያ በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል፡፡

ከስድስት አህጉራት የተውጣጡ 32 ብሄራዊ ቡድኖች የሚካፈሉበትን የአለም ዋንጫ በስኬት ለማጠናቀቅ ሀገራት ወደ ስፍራው ከማቅናታቸው በፊት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የ2018ቱን የሩሲያ አለም ዋንጫ የወቅቱ አሸናፊዋ ጀርመንን ጨምሮ ብራዚል፤ፈረንሳይ፤ስፔን እና እንግሊዝ የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡

የምድብ ድልድሎች፡-
ምድብ ሀ
ሩሲያ ፤ሳውዲ አረቢያ፤ግብፅ እና ዩራጋይ

ምድብ ለ
ፖርቹጋል፤ ስፔን፤ ሞሮኮ እና ኢራን

ምድብ ሐ
ፈረንሳይ፤አውስትራሊያ፤ፔሩ እና ዴንማርክ

ምድብ መ
አርጄንቲና፤አይስላንድ፤ ክሮሺያ እና ናይጄሪያ

ምድብ ሠ
ብራዚል፤ስዊትዘርላንድ፤ኮስታሪካ እና ሰርቢያ

ምድብ ረ
ጀርመን፤ሜክሲኮ፤ ስዊዲን እና ደቡብ ኮሪያ

ምድብ ሰ
ቤልጀም፤እንግሊዝ ፤ቱኒዚያ እና ፓናማ

ምድብ ሸ
ፖላንድ፤ሴኔጋል፤ ኮሎምቢያ እና
ጃፓን ናቸው፡፡

የአለማችን ትልቁን ውድድር እንድታስተናግድ የተመረጠችው ሩሲያ 12 ውብ መጫወቻ ስታዲየሞችን አዘጋጅታለች፡፡

ከእነዚህ ስታዲየሞች መካከል ጥቂቱን እንመልከት፡፡

1.ሉዝኒኪ ስታዲየም፡-

ሀገሪቱ ከገነባቻቸው ስታዲየሞች በግዝፈቱ ቀዳሚ የሆነው ሉዝኒኪ ስታዲየም 80ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

በዘንድሮው አለም ዋንጫም ሩሲያ ከሳውዲ አረቢያ የሚያደርጉትን የመክፈቻ ጨዋታ፤የፍጻሜ ጨዋታ እና ሌሎች የምድብ እና የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎቸን ያስተናግዳል፡፡

2.ሴንት ፒተርስበርግ ስታዲየም፡-

በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የሚገኘው ይህ ስታዲየም 67ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ያለው ግዙፍ ስታዲየም ነው፡፡

የአፍሪካ ተወካዮቹ ናይጄሪያ ከአርጀንቲና፤ሞሪኮ ከኢራን እና ግብፅ ከሩሲያ የሚያደርጉትን የምድብ ጨዋታዎች ያስተናግዳል፡፡

ለደረጃ የሚደረግ ጨዋታም በዚሁ በሴንት ፒተርስበርግ ስታዲየም እንደሚደረግ መርሀ ገብር ተይዞለታል፡፡

3.ፊሽት ስታዲየም፡-

በሶቺ ከተማ የሚገኘው ፊሽት ስታዲየም ሩሲያ ለ2018ቱ አለም ዋንጫ ያሰናዳችው ሌላው ውብ ስታዲየም ሲሆን በተለይ በጉጉት የሚጠበቀውን ፖርቹጋል ከስፔን የሚያደርጉትን የምድል ለ ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡

እኤአ 2013 በይፋ የተመረቀው ፊሽት ስታዲየም 48ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው፡፡

4.ኤካተሪንግ አሬና ስታዲየም፡-

እኤአ 1957 ለጨዋታ ክፍት የሆነው ኤካተሪንግ ግብፅ፤ዩራጋይ፤ፈረንሳይ ከፔሩ፤ሴኔጋል ከጃፓን የመሳሰሉ ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን 45ሺህ ተመልካች እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

5.ቮልጎ ግራድ ስታዲየም፡-

ለአለም ዋንጫው አዲስ ከተገነቡ ስታዲየሞች አንዱ ሲሆን 45 ሺህ ተመልካች ይይዛል፡፡

ቮልጎ ግራድ ስታዲየም ከሚያስተናግዳቸው ጨዋታዎች መካከል እንግሊዝ ከአፍሪካዊቷ ሀገር ቱኒዚያ የሚያደርጉት የምድብ ግጥሚያ ይገኝበታል፡፡

6.ካሊኒንግራድ ስታዲየም፡-

ይህ ስታዲየም በ2018 ግንባታቸው ከተጠናቀቁ አዲስ ስታዲየሞች አንዱ ሲሆን ተመልካች የመያዝ አቅሙም አነስተኛ ነው፡፡

ካሊኒንግራድ ስታዲየም 35ሺህ 212 መቀመጫዎች ብቻ ተገጥመውለታል፡፡

አነስተኛ ስታዲየም ቢሆንም በምድብ 7 እንግሊዝ ከቤልጅየም የሚያደርጉትን ታላቅ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

እንደ ስታዲየም ጋይድ ሪፖርት ገለፃ 12ቱም ስታዲየሞች በአማካይ ከ5 ጨዋታዎች በላይ ያስተናግዳሉ፡፡

እኤአ 1930 ጀምሮ አለም ዋንጫ ያሸነፉ ሀገራት፡፡

1.ዩራጋይ(1930)

2.ጣሊያን(1934)

3.ጣሊያን(1938)
-1942)በሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያት አልታካሄደም
-(1946) በሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያት አልታካሄደም

4.ዩራጋይ (1950)

5.ጀርመን (1954)

6.ብራዚል (1958)

7. ብራዚል(1962)

8. እንግሊዝ (1966)

9.ብራዚል (1970)

10.ጀርመን(1974)

11..አርጀንቲና(1978)

12..ጣሊያን(1982)

13..አርጀንቲና(1986)

14..ጀርመን(1990)

15..ብራዚል(1994)

16..ፈረንሳይ(1998)

17..ብራዚል(2002)

18. ጣሊያን (2006)

19.ኛ ስፔን (2010)

20.ጀርመን (2014)

የ21ኛው የአለም ዋንጫ አሸናፊው ማን ይሆን …?

ምንጭ፡ስታዲየም ጋይድ እና ቶፕ ኢንድ ስፖርት ድረ ገጾች

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here