ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅግጅጋ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በርካታ ህዝብ ደማቅ አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን፤ በዚያውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ያላቸውን ምኞት ገልጸውላቸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያ የስራ ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ከፍተኛ አመራር ያካተተ የልዑካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጀመሪያ የስራ ጉብኝታቸው በክልሉ የተከናወኑትን የመሰረተ ልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ፤ ከህዝቡ ጋርም ውይይት ያደርጋሉ።

በቅርቡ በኦሮሚያና ሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን ያጋጨው ያልተገባ ክስተት በአፋጣኝ በእርቀ ሰላም እንዲፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ።

በዛሬው ዕለት በሱማሌ ክልል የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሉ ህዝብ ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በቅርቡ የኦሮሚያና ሱማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት “ያልተገባ፣ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠና የሁላችንንም አንገት ያስደፋ የሽንፈት ታሪካችን ነው” ብለዋል።

በግጭቱ ሁለቱም ወገን ተሸናፊ እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ያለፈውን ችግር የምንቋቋምበት የዳበረ የአብሮነት ባህል እንዳለም ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here