ይድረስ ለተከበሩ ታጋይ አቶ አስመላሽ ወ/ሥላሴ፦ ዶ/ር ኡብይ እርስዎ ባሰቡበት አውድ “Populist” አይደሉም! -ጌታሁን ሄራሞ (ኬሚካል ኢንጂነር)

የተከበሩ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በመለስ ዜናዊ 6ኛ ዝክረ ዓመት ላይ ያቀረቡትን የውይይት ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተከታትዬአለሁ።

በዚሁ መድረክ ላይ አቶ አስመላሽ በዶ/ር አብይ አመራር ላይ ያላቸውን ዕይታ ከመለስ ጋር እያነፃፀሩ በገደምዳሜም (Obliquely) ቢሆን አንስተዋል።

ለምን አነሱት? የሚል ጥያቄ የለኝም፣ ነገር ግን በተለይም የዶ/ር አብይን አመራር ለመንቀፍ

የሄዱበትን መንገድ ስናጤነው በተነሱ ፅንስ ሐሳቦች ዙርያ ያላቸው ግንዛቤ ወቅታዊን እሳቤ ያማከለ አይደለም።

የወቅታዊ ዕይታዎች(Contemporary Views እክል የብዙዎች ፖለቲከኞቻችን ሥር የሰደደ ችግር ስለመሆኑም እዚህ ጋ ሳልጠቅስ አላልፍም።

ለምሳሌ፦

አቶ አስመላሽ በተዘዋዋሪም ቢሆን የዶ/ር አብይ የአመራር ዕሳቤ ሕዝበኝነት(Populism) ላይ የተንጠለጠለ ስለመሆኑ ጥቆማ ሰጥተዋል።

ቀጥለውም የመለስ ዜናዊን አባባል እየጠቀሱ የሕዝበኝነት ባሕርያትን እንደዚህ ሲሉ ዘረዘሩ፦ “ህዝብን በማይበላ ባዶ ዳቦ ይደልላል።

ህዝበኝነት – የህዝብን ቀልብ ለመሳብ ስሜትን እየኮረኮሩ confusion በመፍጠር የሚካሄድ አስተሳሰብ ነዉ።

በብዥታና በማይጨበጥ ነገር፥ እርስበራሱ የሚጣረስ ንግግር እያደረጉ ህዝብን ማደናገር ነዉ።

ህዝበኝነት ጸረ-ሰላም፥ ጸረ-ዲሞክራሲ፥ ጸረ-ልማት ነዉ። ኋላቀርና አድሀሪነት ነዉ።

መጨረሻዉም ጥፋት ነዉ። ለህዝብ ትክክለኛ የሆነዉን ንገረዉ፥ ትክክለኛ ያልሆነዉም ንገረዉ፥ ነጭ ከሆነ ነጭ ነዉ፥ ቀይ ከሆነ ቀይ ነዉ ብለህ።”

ከዚህም ባለፈ አቶ አስመላሽ የዶ/ሩ ንግግሮች ተራ ስብከት እንደሆኑም ተናግረዋል።

የኔ ጥያቄዎች፦

# ዕውን የአብይ አመራር “Populist” ነው? የ”populist” መሪ የአመራሩ መገለጫ ምንድነው?

በነገራችን ላይ በጊዜ ሂደት ትርጉማቸው እየተለዋወጠ ከመጡ ፅንሰ ሐሳቦች አንዱ “populism” ነው።

For the time being, Let us pause on the contemporary definitions of populism and stick to the old meaning.

የ”The Global rise of Populism” መፅሐፍ ደራሲ ቤንጀሚን ሞፊት ቀደም ሲል የሕዝበኝነትን የአመራር ስልት ይከተሉ የነበሩ መሪዎች አንዱ መገለጫቸው

ትኩረታቸውን ወደ ሰፊው ሕዝብ በማጋደል ሊሂቃንን ከጨዋታ ውጪ ማድረግ ነው ይለናል፦ A classic divide between ‘the people’ and ‘the elites’.

ሌላው የ”Populism” ፅንሰ ሐሳብ ተንታኝ Jan-Wermer Muller ደግሞ ሕዝበኝነትን የሚከተሉ ቀደምት መሪዎች አካታች እንዳልሆኑ ያስታውሰናል፦

“Populists do not just thrive on conflict and encourage polarizations ; they also treat their political opponents as “enemies of people” and seek to exclude them altogather.

ይህ ማለት “populists” አሳታፊ ባለመሆናቸው ኢ-ዲሞክራትክ ናቸው ማለት ነው። አቶ አስመላሽም “populists” ፀረ ዲሞክራትክ ናቸው ያሉት ከዚሁ ተነስተው ነው።

ልብ አድርጉልኝ ከላይ የተቀመጡ የ”populism” ባሕርያት የዱሮዎቹ “populist” መሪዎች ባሕርያት ናቸው።

በአቶ አስመለሽ “labelling” ሳይሆን በነዚህ በዘርፉ ጠበብት መስፈርት እንኳን ዶ/ር አብይን ብንመዝነው

የእርሱ የመሪነት አይዶሎጂ “populist” እንዳልሆነ በቀላሉ ማጤን ይቻላል። ምክንያቱም፦

1. ዶ/ር አብይ ባለፉት ጥቂት ወራት በሕዝብና በሊሂቃን መካከል ክፍፍል ሲፈጥር አላየንም።

እርሱ እንደ “populists አግላይ ሳይሆን አሳታፊ መሆኑን ተመልክተናል።

ከዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ አመለከካታቸው በነ አቶ መለስ የተባረሩትን ወደ ሥራቸው የመለሰው ማን ነበር?

እንዲያውም ለእኔ populist መለስ እንጂ አብይ አይደለም፣ ምናልባት ወደ ፊት በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃዬን አደራጅቼ ብቅ እል ይሆናል።

2. እስቲ ዶ/ር አብይን በ”Jan-Wermer Muller”ገለፃ መሠረት ደግሞ እንፈትሸው።

ዶ/ር አብይ እውን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያገለለ የሕዝብን ፍቅር የሚያስስ መሪ ነው? እንዴት ተብሎ?

ማን ነበር ተቃዋሚ የሚለውን ስያሜ “ተፎካከሪ” ብሎ የቀየረው? ማን ነበር “አሸባሪ” ተብለው በየሀገሩ የተበተኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደገና ጠርቶ የሰበሰባቸው? መለስ ወይስ አብይ?

አሁንም እደግመለሁ መለስ ለእኔ ድብቅ “populist” ነው።

ሁሌም ምርጫ ሲቃረብ ተስፋው 80-85% ገበሬው ነበር።

ሊሂቃኑና ከተሜው በፖለቲካው ገበያው፣ በምርጫው ሜዳ አዋጪ እንዳልሆኑ በግልፅ ያውቅ ነበር።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም እንዴት አድርጎ ማሽመድመድ እንደሚቻል ማን ነበር ያሳያን?

እስቲ አሁን ደግሞ ወደ ወቅታዊው የ”populism definition” እንምጣ። “populism”ን እነ አቶ አስመላሽ በነባሩና በቀደምት ትርጉሙ ቢያብጠለጥሉትም የዛሬው ትርጓሜ ሌላ ነው።

ዛሬ “populism” ፀረ ዲሞክራትክ አይደለም፣ እንዲያውም ይህ አሁን ያለንበት ዘመን ፖለቲካ ወደ “populism” ያጋደለ እንደሆነ ብዙዎቹ ተመራማሪዎች በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ።

ይህን በተመለከተ ካላይ የጠቀስኳቸው ደራሲ ቤንጀሚን እንደዚህ ይላሉ፦

“…Populism today has changed and developed from its earlier iterations, embedded as it is within a rapidly shifting political and media communications landscapes.

እንዲያውም Jean-Warmer በ “What is Populism? መፅሐፋቸው”Pink Tide” ተብሎ በሚጠራው ንቅናቄ ውጤታማ ስለሆኑ ሦስቱ “populist” የላቲን አሜሪካ መሪዎች አንስተዋል፣

እነርሱም Rafael Correa(Equador), Evo Morales(Bolivia), Hugo Chavez(Venuzuela) ናቸው።

ይህን ያነሳሁት አቶ አስመለሽ እንዳነሱት “populism”ን አቶ መለስ ስላወገዙት ብቻ ወደ ዳር የሚገፈተር ሳይሆን ዘመናዊውን አውድ ተከትሎ ሊተገበር የሚችል የፖለቲካ ስትራቴጂ ስለመሆኑም ለመጠቆም ያክል ነው።

በነገራችን ላይ አንዳንድ የአመራር ስልታቸው ባይጥመኝም ዶናልድ ትራምፕም “Populist” መሪ እንደሆኑ ይነገራል።

እናም በአቶ አስመላሽ ገለፃ መሠርት አሜሪካ በpopulist መሪ እየተመራች ስለሆነ ፀረ-ዲሞክራት ነች ማለት ነው?

ፀረ ሰላም፤ ፀረ-ልማት ነች ማለት ነው? የተከበሩ አቶ አስመላሽ፦ ብዙ ጥንት ዩምናውቃቸው ፅንሰ ሐሳቦች ጥንት ባሉበት የግንዛቤ መደብ ላይ የሉም። ትርጉማቸው ሁሌም በለውጥ ሂደት ላይ ነው፣

እኛም የለውጡ አካል ካልሆንን የጥንቱን ስናቀነቅን ትዝብት ላይ እንወድቃለን፣ እናም ዶ/ር አብይ በየትኛውም መስፈርት በእርስዎ በጥንታዊ ትርጓሜ መሠረት “Populist” አይደለም።

ንግግሮቹም ቢሆኑ መሠረታዊውን የ”Rhethoric” ጥበብን የተጎናፀፉ ንግግሮች እንጂ ተራ ስብከቶች አይደሉም።

ከአክብሮት ጋር!

ጌታሁን ሄራሞ (ኬሚካል ኢንጂነር)

***

ታጋይ አስመላሽ_ወልደሥላሴ በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ጉዳዮች ተጠሪ ሚንስትር

ዝክረ-መለስ 6ኛ ዓመትን በማስመልከት ካቀረቡት የመነሻ ሀሳብ የተወሰደ

በጥሩ ንግግር ና ስብከት ኣገር ማስተዳደር ኣይቻልም ።

Posted by Negasi Gebreab on Sunday, August 19, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here