ይህ  በምስሉ ላይ ከሐመሮች ጋር እየተላቀሰ የሚታዬው የ ” ከቡስካው በስተጀርባ” ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ነው።

ደራሲው ለምን ይሆን ሐመሮች ጋር እንዲህ የሚላቀሰው? የፎቶው ባለቤት ጥበቡ በለጠ ምክንያቱን እንደሚከተለው በአጭሩ ይነግረናል :-

ፍቅማርቆስ ደስታ የሐመር ብሔረሰብ የጡት ልጅ ነው፡፡

ይህ ማለት በስጋ ሳይዋለዳቸው የብሔረሰቡ ሙሉ በሙሉ አባል ሆኗል፡፡ ፍቅረማርቆስ ሐመር ነው፡፡

በሐመሮች ፍቅር ወድቆ፣ እነሱም በሱ ፍቅር ወድቀው፣ የጎጃሙ ጉብል ከሐመር ጋር በፍቅር ተሳሰረ፡፡

ፍቅረማርቆስ ሐመር ውስጥ የመንፈስ አባት አለው፡፡ ቤተሰብ አለው፡፡ ወንድምና እህቶች አሉት፡፡

አክስት፣አጎት ሁሉም የቤተሰብ አባላት አሉት፡፡ እናም በ2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ከደቡብ ክልል ጋር በመተባበር “ሕያው የጥበብ ጉዞ ወደ ከቡስካ በስተጀርባ ድንግል ሐገር ውበት” በሚል ርዕስ ጉዞ አዘጋጅቶ ነበር፡፡

በዚያ ጉዞ ላይ 56 ብንሆንም አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ ሐመር ስንደርስ የብሄረሰቡ አባል የሆነውና የፍቅረማርቆስ ደስታ የመንፈስ ወንድም የሆነው ወጣቱ ኮሌ አይታ በህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡

ፍቅረማርቆስ ደስታ ወደ ሐመር ሲመጣ ወንድሙ መጣ ተብሎ ቱርሚ ቀውጢ ሆነች፡፡ ለቅሶው በረታ፡፡

የኮሌ ወንድም ፍቅረማርቆስ መጣ ተብሎ ሐመሮች ተሰብስበው አለቀሱ፡፡ እኔም በዚያን ወቅት እያለቀስኩ እነዚህን ታሪካዊ ፎቶዎች አነሳሁ፡፡

ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ከዚህ ፍቅር ውስጥ ነው ወጥቶ የሄደው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here