አባት ሴት ልጁን ገደለ

በደሴ ከተማ ፡ ሳላይሽ አካባቢ አንዲት የ7 ዓመት ሕጻን ተገድላ ተገኘች

ሕጻኗ ተገላ የተገኘቸው ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ሳላይሽ አካባቢ አስከሬንዋ በኬሻ ተጠቅልሎ መገኘቱን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የህጻኟ ወላጅ እናት ወ/ሮ አበባ ሙህየ ሟች ልጇ ከቅዳሜ ጥቅምት 24 አራት ሰዓት ጀምሮ በመጥፋትዋ በፖሊስና በአካቢው ነዋሪዎች ስትፈለግ ብትቆይም በህይወት ሳይሆን ተገላ መገኘትዋን ተናገራለች፡፡

ድርጊቱን የፈፀመው ወንጀለኛ እንጀራ አባቷ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንደሰን ጸጋዬ፤ ‹‹ድርጊቱ በጣም አሳዛኝ ነው፤

ፖሊስም ድርጊቱ እንደተሰማ ወዲያውኑ አጣሪ ግብረ ኃይል በማቋቋም ዋና ተጠርጣሪ የተባለውን ግለሰብና ሁለት ግብረ አበሮችን መያዙን ገልጸው የምርመራውን ሂደት ወደፊት ይፋ ይደረጋል፤ ህብረተሰቡም ለምርመራ መሳካት እንዲረጋጋ ጠይቀዋል፡፡

በርካታ የአካቢውና የከተማው ነዋሪ አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋል፡፡

ወንጀሉን ለማውገዝ የወጣው ሕዝብ ፤ ‹‹በስቅላት ይቀጣ ፤ በሕዝብ ፊት አስተማሪ እርምጃ ይወሰድበት ፤

ይህን መሠሉ የጭካኔና ኢ ምራላዊ ተግባር የሕዝባችንን አኩሪ ባህልና እሴት የሚሸረሽር ነው፡፡ ደሴዎች ይሄን አንታገስም! …ወዘተ ›› ሲል ፤ ድምፁን እያሰማ ነው፡፡

መንገድ ተዘግቶ ነበር፡፡ ታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡:

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here