ዮናስ አብርሀምና በረከት አብረሃም ሁለቱም ከአንድና ከአንድ አባት የወጡ ወንድማማቾች ናቸው ።

በስራቸውም ሁለቱም ጋዜጠኞች ናቸው ።

ዮናስ እማማ ጨቤ በሚል ብዙዎቻችን የምናቀው ተወዳጅ የራዲዮ ድራማ ደራሲ ነው::

እንዲሁም ልብ ለልብ በሚል የሚታወቀው የፍቅር ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የራዲዮ ድራማ ደራሲና ሁለት መጻህፍትንም ለአንባቢያን አድርሷል ።

ቀደም ሲል በፋና አሁን ደግሞ በብስራት ራዲዮ እየሰራ ይገኛል። 

በረከት አስመራ ላይ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነው:: ምንም እንኳን በመረጃ እጥረት ስራውን ማቅረብ ባልችልም::

ዮናስ ኢትዮጵያ ሲሆን በረከት ኤርትራዊ ነው ። አንዳቸው አዲስ አበባ ላይ አንዳቸው አስመራ ላይ በጋዜጠኝነት ተሰማርተው ።

ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ ተለያይተው የተገናኙት በቅርቡ ነው::

በረከት ልጆቹን ይዞ የኤርትራን ደንበር አቋርጦ ጥይትና አስቸጋሪውን መንገድ አቋርጦ ወደ ኢትዮጲያ በመግባቱ በልጅነት የተለያዩ ወንድማማቾች ተገናኝተው በእንባ ተራጭተው ፈጣሪን አመስግነዋል ።

ሆኖም ደስታቸው ሙሉ አይደለም:: ምክንያቱም ያሳለፋት ነገር በቀላሉ በቃላት የሚገለጽ አይደለም::

በረከት እንዳለው ዮናስ አባቱን ሳያያቸው እሱን እንዳሉ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

እናታቸው ግን አሁንም ልጃቸውን እንደናፈቁ አሱን በአይነ ስጋ ለመተያየት አብቃን እያሉ አየጸለዩ በኤርትራ ይኖራሉ ።

ዮናስም እናቴ ናፍቃኛለች እባካችሁ ድንበሩን ከፈቱትና ልያት እዚሁ ቅርብ ሆና ሳላያት አንድ ነገር ቢፈጠር ጸጸቱንን አልችለውም ብሏል ።

የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ከፖለቲካ በላይ ነው በሁለት መንግስት የሚተዳደሩ የአንድ ህዝቦች ጉዳይ ነው ።

እስኪ በነዮናስ ቦታ ሁነን ጉዳዩን ለደቂቃ እንመልከተው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here