ዶክተር ካትሪን በኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታሎችን በመመሰረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ  የሕክምና እንዲሁም የሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት በመቶሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችን ሕይወት ታድገዋል።

የክብር ዜግነቱን የሰጡት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ የተወለዱ ናቸው።

በአዲስ አበባ  በቀድሞው የልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል በአሁኑ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ሆስፒታል የአዋላጅነት ትምህርት ቤት ለመምህርነት በኢትዮጵያ መንግሥት የወጣውን የሥራ ማስታወቂያ አልፈው  እኤአ በ1959 ሥራ ጀምረዋል።

ሚያዚያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. የፌስቱላ ሆስፒታል መሥራችና ባለቤት ለሆኑት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የክብር ዜግነት አግኝተዋል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here