ዶ/ር ግርማይ ሃጎስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ እ.ኤ.አ በ1961 ተወለዱ፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዛው ማጨው ከተማ ተምረዋል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እ.ኤ.አ ከ1981-1986 ድረስ በኩባ ሃገር ተከታትለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ1990-1994 የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ህክምና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የተከታተሉ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2004-2007 ድረስ በ sub-specialty of Thorax & Vascular Surgery በሜክሲኮ ሃገር Guadalajara University ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ዶ/ር ግርማይ ሃጎስ እ.ኤ.አ ከ1987-1990 በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በጠቅላላ ሃኪም፣ ከ1995-2000 ድረስ በዋይጨው ሆስፒታል በጠቅላላ ቀዶ ጥገና ሃኪም እንዲሁም ሜዲካል ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2001-2004 ድረስ በመቀሌ ሆስፒታል የጠቅላላ ቀዶ ጥገና ሃኪም እና የስራ ክፍሉ ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡

ዶ/ር ግርማይ ሃጎስ እ.ኤ.አ ከ2007-2009 ድረስ በመቀሌ ሆስፒታል እንዲሁም ከ2009-2018 በመቀሌ ዩንቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ትምህርት ክፍል በጠቅላላ ሃኪም እና Thorax & Vasclar Surgeon ሆነው አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር ግርማይ ባሳለፏቸው የስራ ዘመናት ያካበቱትን ሙያዊ እውቀትና ክህሎት ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉ አዲስ የጤና ባለሙያዎች በማካፈል እንዲሁም በክልሉ ደህንነቱን የጠበቀ የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲስፋፋ በማስተባበር የመሪነት ሚናቸውን ተጫውተዋል፡፡

ዶ/ር ግርማይ ሃጎስ በተለያዩ የሙያ ማህበራት አባል ሆነው በማገልገል ላይ ሲሆኑ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ የተለያዩ ኮንፈረሶች ተሳትፈዋል፡፡

በሙያ መስካቸውም ሰባት በሚሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ምርምርና ጥናት አካሂደዋል፡፡

ከትግራይ ጤና ጥበቃ ቢሮ ለረጅም ጊዜ አገልግሎታቸው ሸልማት ያገኙ ሲሆን በገጠር አካባቢዎች የህክምና ትምህርትን እና የቀዶ ጥገና ህክምናን በመስጠት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ የቀዶ ጥገና ሃኪሞች ማህበር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Girmay Hagos Araaya,  Thoracic Surgeon, Mekelle University

Dr. Girmay Hagos Araaya is an Ethiopian General and thoracic surgeon at Mekelle University college of medicine and health science. He is also a Senior Mentor of Safe Surgery 2020.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here