/የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

እንስቷ የካቢኔ አባል እና የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በመስሪያቤታቸው ሊተገብሯቸው ከሚገቡ በርካታ ስራዎች ውስጥ በ100 ቀናት እቅዳቸው ሊካተቱ የሚገቡ በሚል ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት የዶ/ር ፍፁም መስሪያ ቤት የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት በእቅዱ እንዲያካተት ተመላክቷል፡፡

– አገራዊ የረጅም ዘመን መሪ የልማት እቅድ ማዘጋጀት

– የልማት ፕሮጀክቶች አመራር የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት
– ሁለተኛውን ዕ.ት.ዕ ዓመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት ማዘጋጀት

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባፀደቀው የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር አዋጅ መሰረት ለተዋቀሩት አዳዲስ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጠቅላይ ሚኒስትርዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለ20 የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡

የቀረበውንም የካቢኔ ሹመት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አዲስ ባዋቀሩት ካቢኔያቸው ውስጥ 10 ሴቶችን ማካተታቸው በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ያደርገዋል፡፡

እጩ የካቢኔ አባላቱ የተጀመረውን የማሻሻያ ስርዓት ዳር የማድረስ አቅም ያላቸውን ከግምት ያስገባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተሿሚዎቹ ሌብነትን ባለመታገስና ቅንነትን በተሞላበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስትሮች ተቋማዊ ለውጡን በተደራጀ እና ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲመሩም ጠይቀዋል፡፡

ስነ ምግባር የተሞላበት የአገልግሎት አሰጣጥና ስብሰባን ቀንሶ ብዙውን ጊዜ ለስራ ማዋል ከተሿሚቹ እንደሚጠበቅም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

የተሿሚዎች ዝርዝር፡-
1.የሰላም ሚኒስትር—————————–ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

2. የአገር መከላከያ ሚኒስትር——————–ኢንጂነር አዒሻ ሙሐመድ

3. የገንዘብ ሚኒስትር—————————–አቶ አህመድ ሺዴ

4. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር———————- ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ

5. የግብርና ሚኒስትር—————————-አቶ ኡመር ሁሴን

6. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር—————ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር

7. የገቢዎች ሚኒስትር —————————ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

8.የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ————-ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ

9.የትራንስፖርት ሚኒስትር———————- ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

10.የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር—–አቶ ጃንጥራር አባይ

11. የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር————ዶ/ር ስለሺ በቀለ

12. የትምህርት ሚኒስትር———————–ዶ/ር ጥላዬ ጌቱ

13. የማዕድና ነዳጅ ሚኒስትር——————-ዶ/ር ሳሙኤል ሁርኮ

14. የጠቅላይ አቃቢ ህግ————————-አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ

15. የጤና ጥበቃ ሚኒስትር———————–ዶ/ር አሚር አማን

16. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር———-ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም

17. የሴቶች፣ህፃናትናወጣቶች ጉዳይ ሚ/ር——–ወ/ሮ ያለም ፀጋይ

18. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር———–ዶ/ር ኢንጎንጌ ተስፋዬ

19. የባህልናቱሪዝም ሚኒስትር ——————-ዶ/ር ሂሩት ካሳው

20. የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር—————ዶ/ር ፍፁም አሰፋ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here