Petros Ashenafi Kebede

ሙባራክ አል ባታሊ የታወቁ ኩዌታዊ የእስልምና መምህር ናቸው።

ባለፈው ቅዳሜ በዩክሬይኗ መዲና ኪየቭ በስፔኑ ሪያል ማድሪድና በእንግሊዙ ሊቨርፑል ክለቦች መካከል በተካሄደው

የ2018 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ሞሃመድ ሳላህ በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ጨዋታውን አቋርጦ ለመውጣት መገደዱ ይታወቃል።

ጉዳቱ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ብቻ ሳይሆን በተለይ ከቀናት በኋላ በሩሲያ በሚጀመረው የአለም ዋንጫ ላይደርስ ይችላል በሚል ስጋት ግብፃውያንን አስከፍቷቸዋል።

ጉዳት ያደረሰበት የማድሪዱ ተከላካይና ካፕቴይን ሰርጂዮ ራሞስንም ፊፋና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ቅጣት እንዲያስተላልፉበት በሚል

በኦንላይን የተከፈው ዘመቻ ከ500 ሺህ በላይ ድምፅ መሰብሰብ የቻለ መሆኑን አለም እየተመለከተው ነው።

ዛሬ ለየት ያለ ጉዳይ ይዞ ወደ ትዊተር የመጣው የኡስታዝ ሙባራክ ኣል ባታሊ መልዕክት ግን አነጋጋሪ ሆኖ ተገኝቷል።

ኡስታዝ እንደሚሉት ሳላህ ታላቁ የረመዳን ፆምን ኳስ ለመጫወት ብሎ ማቋረጡ ስህተት ነው ባይ ናቸው።

እርግጥ ነው ፆምን በጉዞና በህመም ምክንያቶች ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ቅሪላ ለመግፋት ተብሎ መብላትና መጠጣት ትክክል አይደለም ይላሉ።

ለዚህም ሳላህ ፆሙን እንዲያቋርጥ የመከሩትን ይኮንናሉ።

ሳላህም የእስልምናን ህግ ተላልፎ የፍፃሜው ጨዋታ ዕለት ፆም አፍርሶ ወደ ሜዳ በመግባቱ አላህ ርምጃ ወስዶበት በጉዳት ከሜዳ ሊወጣ ችሏል ብለዋል።

“ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህ ላይ የደረሰው ጉዳት ፆም በማቋረጡ ከአላህ የመጣ ቅጣት እንጂ ከሰርጅዮ ራሞስ አይደለም ሼህ ሙባራክ አል ባታሊሳላህ ከፍፃሜው ጨዋታ ሁለት ቀናት ቀደን ብሎ በጊዜያዊነት ፆሙን እንደሚያቋርጥ መናገራቸው ይታወሳል

“ሙስሊም በምክንያትና በጥረት የሚመራ አይምሰላሁ ህይወት ለፈቀዳት በእግዚአብሄር እጅ ናት። ምናልባት ይሄ ጉዳትም ለበጎ ሊሆን ይችላል” ብለዋል

ኡስታዝ ለሳላህ ያላቸውንም አድናቆት ገልፀዋል ።

ሳላህ የምዕራቡ አለም አምባሳደራችን ነው የቡድን ጏዶቹ አልኮል በሚጠጡበት ወቅት አብሯቸው ባለመሆን እንዲሁም ጎል ካስቆጠረ በኋላም ለፈጣሪው ሰላት በመስገድ ምስጋና ማቅረቡን እንደሚወዱለት፤

አሁንም የደረሰበትን ጉዳትና የፈፀመውን ቀኖናዊ ስህተት በመረዳት ለንስሃ የፈጣሪው በር ማንኳኳት አለበት ብለዋል።

ሞሃመድ ሳላህ ባሁኑ ጊዜ በስፔን ህክምናውን በመከታተል ላይ ያለ ሲሆን ለ አለም ዋንጫም መድረስ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።

ታላቁ የግብፅ ሙፍቲ ሻውኪ ኣላም በአለም ዋንጫ ግብፅን ወክለው የሚጫወቱ የብሄራዊ ቡዱኑ አባላት ጨዋታ ያላቸው ቀን እንዳይፆሙና ከረመዳን ፍች በኋላ በመፆም እንዲያካክሱ ፈቃድ ሰጥተዋል።

Mohamed Salah Liverpool FC Egypt national football team

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here